Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ኢያሱ 19:50 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

50 በኤፍሬም ተራራማ አገር ያለችውን እንዲሰጡት የጠየቃቸውን ተምናሴራ የምትባለውን ከተማ እንደ ጌታ ትእዛዝ ሰጡት፤ ከተማም ሠርቶ ተቀመጠባት።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

50 እግዚአብሔር ባዘዘውም መሠረት በኰረብታማው የኤፍሬም ምድር የምትገኘውን ተምናሴራ የምትባለውን የፈለጋትን ከተማ ሰጡት፤ እርሱም ከተማዪቱን ሠራ፤ መኖሪያውም አደረጋት።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

50 እግዚአብሔርም ባዘዘው መሠረት በኮረብታማው በኤፍሬም አገር እንዲሰጡት የጠየቃቸውን ቲምናትሴራሕ ተብላ የምትጠራውን ከተማ ሰጡት፤ ያቺንም ከተማ እንደገና ሠርቶ መኖሪያው አደረጋት።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

50 በኤ​ፍ​ሬም ተራ​ራማ ሀገር ያለ​ች​ውን ተም​ና​ሴራ የም​ት​ባ​ለ​ውን የፈ​ለ​ጋ​ትን ከተማ ሰጡት፤ ከተ​ማም ሠርቶ ተቀ​መ​ጠ​ባት።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

50 በኤፍሬም ተራራማ አገር ያለችውን ተምናሴራ የምትባለውን የፈለጋትን ከተማ እንደ እግዚአብሔር ትእዛዝ ሰጡት፥ ከተማም ሠርቶ ተቀመጠባት።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ኢያሱ 19:50
6 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

የእነዚህም ዐሥራ ሁለት የክፍላተ ሀገር ገዢዎችና የሚያስተዳድሩአቸውም ግዛቶች ስም ዝርዝር ከዚህ የሚከተለው ነው፥ ቤንሑር፦ ኰረብታማ የሆነችው የኤፍሬም አገር ገዢ፤


ሴት ልጁም ታችኛውንና ላይኛውን ቤት-ሖሮንንና ኡዜን-ሼራን የሠራች ሲኦራ ነበረች።


ከኤፍሬም ነገድ የነዌ ልጅ ሆሴአ፤


ምድሩንም ሁሉ በየግዛቱ ርስት እንዲሆን አከፋፍለው ከጨረሱ በኋላ፥ የእስራኤል ልጆች ለነዌ ልጅ ለኢያሱ በመካከላቸው ርስት ሰጡት።


በተራራማው በኤፍሬም አገር በገዓስ ተራራ በሰሜን ባለችው በርስቱ ግዛት በተምና-ሴራ ቀበሩት።


እነርሱም በኰረብታማው በኤፍሬም አገር በምትገኘው ከገዓስ ተራራ በስተ ሰሜን ባለችው በራሱ ርስት ላይ በቲምናሔሬስ ቀበሩት።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች