Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ኢያሱ 19:26 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

26 አላሜሌክ፥ ዓምዓድ፥ ሚሽአል ነበረ፤ በምዕራብ በኩል ወደ ቀርሜሎስና ወደ ሺሖር-ሊብናት ደረሰ፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

26 አላሜሌክ፣ ዓምዓድ እንዲሁም ሚሽአል። ድንበሩ በስተ ምዕራብ ቀርሜሎስንና ሺሖርሊብናትን ይነካል፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

26 ኣላሜሌክን፥ ዓምዓድንና ሚሽአልን ይጨምራል፤ በምዕራብም ከቀርሜሎስና ከሺሖርሊብናት ይዋሰናል፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

26 አሊ​ሜ​ሌክ፥ አሜ​ሕል፥ ማሕሳ ነበር፤ በባ​ሕ​ርም በኩል ወደ ቀር​ሜ​ሎስ፥ ወደ ሴዎ​ንና ሊበ​ናት ይደ​ር​ሳል፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

26 አላሜሌክ፥ ዓምዓድ፥ ሚሽአል ነበረ፥ በምዕራብ በኩል ወደ ቀርሜሎስና ወደ ሺሖርሊብናት ደረሰ፥

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ኢያሱ 19:26
15 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ምድሪቱ አለቀሰች ከሳችም፤ ሊባኖስ አፈረ ጠወለገም፤ ሳሮን እንደ ምድረ በዳ ሆነ፤ ባሳንና ቀርሜሎስ ቅጠላቸውን አረገፉ።


ራስሽ እንደ ቀርሜሎስ ተራራ በላይሽ ነው፥ የራስሽም ጠጉር እንደ ሐምራዊ ሐር ነው፥ ንጉሡ በሹርባው ታስሮአል።


አክዓብ እህልና ውሃ ለመቅመስ ሲሄድ፥ ኤልያስ ወደ ቀርሜሎስ ተራራ ወጣ፤ እዚያም በሁለቱ ጉልበቶቹ መካከል ራሱን ወደ መሬት ደፋ።


ስለዚህም አክዓብ ለእስራኤላውያን ሁሉና ለነቢያት በሙሉ ጥሪ አድርጎ በቀርሜሎስ ተራራ እንዲሰበሰቡ አስደረገ።


እኔ ሕያው በመሆኔ ይላል ስሙ የሠራዊት ጌታ የተባለው ንጉሥ፥ በተራሮች መካከል እንዳለ እንደ ታቦር፥ በባሕርም አጠገብ እንዳለ እንደ ቀርሜሎስ፥ እንዲሁ በእውነት ይመጣል።


አንተም እንዲህ አለክ፦ በሠረገላዬ ብዛት ወደ ተራሮች ከፍታ፥ ወደ ሲባኖስ ጥግ ወጥቻለሁ፤ ረጃጅሞቹን ዝግባዎች፥ የተመረጡትን ጥንዶች እቈርጣለሁ፥ ወደ ከፍታውም ዳርቻ ወደ ቀርሜሎስ ዱር እገባለሁ፤


እጅግ ያብባል በደስታና በዝማሬ ሐሤትን ያደርጋል፤ የሊባኖስ ክብር፥ የቀርሜሎስና የሳሮን ግርማ ይሰጠዋል፤ የጌታንም ክብር የአምላካችንንም ግርማ ያያሉ።


ከአሴርም ነገድ መዓሳልና መሰማሪያዋ፥ ዓብዶንና መሰማሪያዋ፥


ሳሙኤልም ጠዋት ተነሥቶ በማለዳ ሳኦልን ለመገናኘት ሄደ፤ ነገር ግን፥ “ሳኦል ወደ ቀርሜሎስ ሄዷል፤ ለራሱ ክብር የመታሰቢያ ሐውልት በዚያ ካቆመ በኋላ ተመልሶ ወደ ጌልገላ ወርዷል” ተብሎ ተነገረው።


ከአሴርም ነገድ ሚሽአልንና መሰማሪያዋን፥ ዓብዶንንና መሰማሪያዋን፥


ድንበራቸውም ሔልቃት፥ ሐሊ፥ ቤጤን፥ አክሻፍ፥


ወደ ፀሐይም መውጫ ወደ ቤትዳጎን ዞረ፥ ወደ ዛብሎንም ወደ ይፍታሕኤል ሸለቆ፥ በሰሜን በኩል ወደ ቤት-ዔሜቅና ወደ ንዒኤልም ደረሰ፤ ከዚያም ወደ ሰሜን ወደ ካቡል ወጣ፤


ይልቅስ አሁን እስራኤላውያንን ሁሉ እንዳገኛቸው በቀርሜሎስ ተራራ ሰብስብልኝ፤ በንግሥት ኤልዛቤል ማእድ የሚቀለቡትን አራት መቶ ኀምሳ የባዓል ነቢያትንና አራት መቶ የአሼራ ነቢያትን ጭምር ይዘህ ና።”


ማዖን፥ ቀርሜሎስ፥ ዚፍ፥ ዩጣ፥


ኤልሳዕም ወደ ቀርሜሎስ ተራራ ወጣ፤ ዘግየት ብሎ ግን ወደ ሰማርያ ተመለሰ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች