Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ኢያሱ 11:23 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

23 ጌታም ለሙሴ እንደ ተናገረው ሁሉ ኢያሱ ምድሪቱን ሁሉ ያዘ፤ ኢያሱም ለእስራኤል እንደየነገዳቸው ድርሻ ርስት አድርጎ ምድሪቱን ሰጣቸው፤ ምድሪቱም ከጦርነት ዐረፈች።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

23 ስለዚህ ኢያሱ እግዚአብሔር ሙሴን ባዘዘው መሠረት ምድሪቱን በሙሉ ያዘ፤ እንደ ነገዳቸው አከፋፈል በመመደብም ርስት አድርጎ ለእስራኤላውያን ሰጣቸው። ከዚያም ምድሪቱ ከጦርነት ዐረፈች።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

23 እግዚአብሔር ሙሴን ባዘዘው መሠረት ኢያሱ ምድሩን ሁሉ በእጁ አደረገ፤ ለእያንዳንዱ ነገድ አንዳንድ ድርሻ ርስት አድርጎ በመስጠት ለእስራኤላውያን በሙሉ አከፋፈለ። ስለዚህም ምድሪቱ ከጦርነት ዐረፈች።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

23 እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ለሙሴ እን​ዳ​ዘ​ዘው ሁሉ ኢያሱ ምድ​ሪ​ቱን ሁሉ ያዘ፤ ኢያ​ሱም ለእ​ስ​ራ​ኤል እንደ ክፍ​ላ​ቸው በየ​ነ​ገ​ዳ​ቸው ርስት አድ​ርጎ ምድ​ሪ​ቱን ሰጣ​ቸው፤ ምድ​ሪ​ቱም ከጦ​ር​ነት ዐረ​ፈች።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

23 እግዚአብሔርም ለሙሴ እንደ ነገረው ሁሉ ኢያሱ ምድሪቱን ሁሉ ያዘ፥ ኢያሱም ለእስራኤል እንደ ክፍላቸውና እንደ ነገዳቸው ርስት አድርጎ ምድሪቱን ሰጣቸው፥ ምድሪቱም ከሰልፍ ዐረፈች።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ኢያሱ 11:23
20 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ልጆቹም ገብተው ምድሪቷን ወረሱ፤ የምድሪቱን ሰዎች ከነዓናውያንን በፊታቸው ደመሰስካቸው፥ የወደዱትን ነገር እንዲያደረጉባቸው ከነገሥታቶቻቸውና ከምድሪቱ ሕዝቦች ጋር በእጃቸው አሳልፈህ ሰጠሃቸው።


የጌታን ሥራ፥ በምድር ያደረገውንም ተኣምራት እንድታዩ ኑ።


ዛሬ የማዝዝህን ነገር ጠብቅ፤ እነሆ እኔ አሞራዊውን፥ ከነዓናዊውን፥ ኬጢያዊውን፥ ፌርዛዊውን፥ ኤዊያዊውንና ኢያቡሳዊውን በፊትህ አወጣለሁ።


ይህም ከምድሪቱ በእስራኤል ዘንድ ርስት ይሆንለታል፥ መሪዎቼ ሕዝቤን ከእንግዲህ ወዲህ አያስጨንቋቸውም፥ ነገር ግን ምድሪቱን ለእስራኤል ቤት እንደ ነገዳቸው ይሰጡአቸዋል።


በፊትህ የሚቆመው የነዌ ልጅ ኢያሱ ወደዚያ ይገባል፤ እርሱ ለእስራኤል ምድሪቱን ያወርሳልና አበረታታው።’


ጌታ እግዚአብሔር ርስት አድርጎ በሚሰጥህ ምድር ዙሪያ ካሉት ጠላቶችህ ሁሉ ባሳረፈህ ጊዜ፥ ከሰማይ በታች ያለውን የአማሌቅን መታሰቢያ መደምሰስን፥ ይህንን አትርሳ።”


ኢያሱም ብዙ ዘመን ከእነዚህ ነገሥታት ሁሉ ጋር ይዋጋ ነበር።


ኢያሱና የእስራኤል ልጆች ያሸነፉአቸው የምድሪቱ ነገሥታት እነዚህ ናቸው፤ እነርሱም የነበሩት በዮርዳኖስም ማዶ በምዕራብ በኩል በሊባኖስ ሸለቆ ካለችው ከበኣልጋድ ወደ ሴይር ተራራ እስከሚያወጣው እስከ ሐላቅ ተራራ ድረስ ኢያሱ በየድርሻቸው ርስት አድርጎ ለእስራኤል ነገድ በሰጣት ምድር፥


ኢያሱም በጌታ ፊት በሴሎ ዕጣ ጣለላቸው፤ በዚያም ኢያሱ ለእስራኤል ልጆች እንደየድርሻቸው ምድሩን ከፈለ።


እንግዲህ አሁን አምላካችሁ ጌታ እንደ ተናገራቸው ወንድሞቻችሁን አሳርፎአቸዋል፤ ስለዚህ አሁን ተመለሱ፥ ወደ ቤታችሁና የጌታ ባርያ ሙሴ በዮርዳኖስ ማዶ ወደ ሰጣችሁ ወደ ርስታችሁ ምድር ሂዱ።


እንዲህም ሆነ፤ ከብዙ ዘመን በኋላ፥ ጌታም እስራኤልን በዙሪያቸው ካሉት ጠላቶቻቸው ሁሉ ባሳረፋቸው ጊዜ፥ ኢያሱም በሸመገለ ዕድሜውም በገፋ ጊዜ፥


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች