ኢያሱ 10:37 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)37 ያዙአትም፤ እርሷንም ንጉሥዋንም ከተሞችዋንም ሁሉ በእርሷም ያሉትን ሰዎች ሁሉ በሰይፍ ስለት መቱ፤ በዔግሎም እንዳደረገው ሁሉ ማንንም አላስቀረም፤ እርሷንም በእርሷም ያሉትን ሰዎች ሁሉ ፈጽሞ አጠፋ። ምዕራፉን ተመልከትአዲሱ መደበኛ ትርጒም37 ከተማዪቱንም ከንጉሧ፣ ከመንደሮቿና በውስጧ ካሉት ጋራ ሁሉ አንድም ሰው ሳያስቀሩ በሰይፍ ስለት ፈጇቸው፤ በዔግሎን እንዳደረጉት ሁሉ እዚህም ከተማዪቱንና በውስጧ ያለውን ሁሉ ፈጽመው ደመሰሱ። ምዕራፉን ተመልከትአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም37 እርስዋንም ይዘው ንጉሡን፥ በከተማይቱና በአካባቢዋም የገጠር ከተሞች ያገኙትን ሁሉ ገደሉ፤ ኢያሱም ልክ በዔግሎን ባደረገው ዐይነት ከተማይቱ እንድትደመሰስ ፈረደባት፤ በእርስዋም ውስጥ በሕይወት የተረፈ አንድም አልነበረም። ምዕራፉን ተመልከትየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)37 እርስዋንም፥ ንጉሥዋንም፥ ከተሞችዋንም ሁሉ፥ በእርስዋም ያሉትን ነፍሳት ሁሉ በሰይፍ ስለት መቱ፤ በአዶላም እንዳደረገው ሁሉ ማንንም አላስቀረም ፤ እርስዋንም፥ በእርስዋም ያሉትን ነፍሳት ሁሉ ፈጽሞ አጠፋ። ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)37 እርስዋንም ንጉሥዋንም ከተሞችዋንም ሁሉ በእርስዋም ያሉትን ነፍሳት ሁሉ በሰይፍ ስለት መቱ፥ በኦዶላም እንዳደረገው ሁሉ ማንንም አላስቀረም፥ እርስዋንም በእርስዋም ያሉትን ነፍሳት ሁሉ ፈጽሞ አጠፋ። ምዕራፉን ተመልከት |