Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ኢያሱ 10:32 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

32 ጌታም ለኪሶን በእስራኤል እጅ አሳልፎ ሰጣት፥ በሁለተኛውም ቀን ያዙአት፤ በልብናም እንዳደረጉት ሁሉ፥ እርሷን በእርሷም ያሉትን ሰዎች ሁሉ በሰይፍ ስለት መቱአቸው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

32 እግዚአብሔር ለኪሶን አሳልፎ ለእስራኤል ሰጠ፤ ኢያሱም በሁለተኛው ቀን ያዛት፤ በልብና እንዳደረገው ሁሉ እዚህም ከተማዪቱንና በውስጧ ያሉትን ሁሉ በሰይፍ ስለት ፈጃቸው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

32 እግዚአብሔርም ጦርነቱ በተጀመረ በሁለተኛው ቀን ለእስራኤላውያን በላኪሽ ላይ ድልን ሰጣቸው፤ በሊብና ባደረጉትም ዐይነት በከተማይቱ ያገኙትን ሰው ሁሉ በሰይፍ ፈጁ፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

32 እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ላኪ​ስን በእ​ስ​ራ​ኤል እጅ አሳ​ልፎ ሰጣት፤ በሁ​ለ​ተ​ኛ​ውም ቀን ያዙ​አት፤ በል​ብ​ናም እን​ዳ​ደ​ረ​ጉት ሁሉ፥ እር​ስ​ዋን፥ በእ​ር​ስ​ዋም ያሉ​ትን ነፍ​ሳት ሁሉ በሰ​ይፍ ስለት መቱ​አ​ቸው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

32 እግዚአብሔርም ለኪሶን በእስራኤል እጅ አሳልፎ ሰጣት፥ በሁለተኛውም ቀን ያዙአት፥ በልብናም እንዳደረጉት ሁሉ፥ እርስዋን በእርስዋም ያሉትን ነፍሳት ሁሉ በሰይፍ ስለት መቱአቸው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ኢያሱ 10:32
7 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ኢያሱም ዓማሌቅንና ሕዝቡን በሰይፍ ስለት አሸነፈ።


ራፋስቂስም ተመለሰ፤ የአሦርም ንጉሥ ከለኪሶ እንደ ራቀ ሰምቶ ስለ ነበር በልብና ከተማ ሲዋጋ አገኘው።


ጌታ አምላክህም በእጅህ አሳልፎ በሰጣቸውና ድል በምትነሣበት ጊዜ፥ ፈጽመህ አጥፋቸው፥ ከእነርሱም ጋር ቃል ኪዳን አታድርግ፥ አትማራቸውም፥


በዚያም ቀን ኢያሱ መቄዳን ያዛት፥ እርሷንና ንጉሥዋንም በሰይፍ ስለት መታ፤ በእርሷም ያሉትን ሰዎች ሁሉ ፈጽሞ አጠፋቸው፥ ከእነርሱም አንድም እንኳ አላስቀረም፤ በኢያሪኮም ንጉሥ ላይ እንዳደረገው እንዲሁ በመቄዳ ንጉሥ ላይ አደረገ።


ኢያሱም ከእርሱም ጋር እስራኤል ሁሉ ከልብና ወደ ለኪሶ አለፉ፥ ከበቡአትም፥ ወጉአትም።


በዚያን ጊዜም የጌዝር ንጉሥ ሆራም ለኪሶን ለመርዳት ወጣ፤ ኢያሱም አንድም እንኳ ሳይቀር እርሱንና ሕዝቡን መታ።


የጌታም ባርያ ሙሴ እንዳዘዘው፥ ኢያሱ የእነዚህን ነገሥታት ከተሞች ሁሉ፥ ነገሥታቶቻቸውንም ሁሉ ያዘ፥ በሰይፍም ስለት መታቸው፥ ፈጽሞም አጠፋቸው።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች