Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ዮናስ 1:9 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

9 እርሱም፦ “እኔ ዕብራዊ ነኝ፥ ባሕሩንና የብሱን የፈጠረውን፥ የሰማይን አምላክ እግዚአብሔርን አመልካለሁ” አላቸው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

9 እርሱም፣ “እኔ ዕብራዊ ነኝ፤ የብስንና ባሕርን የፈጠረውን የሰማይን አምላክ እግዚአብሔርን አመልካለሁ” አለ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

9 ዮናስም “እኔ ዕብራዊ ነኝ፤ የብስንና ባሕርን የፈጠረውን የሰማይ አምላክ እግዚአብሔርን አመልካለሁ” ሲል መለሰላቸው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

9 እር​ሱም፥ “እኔ ዕብ​ራዊ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ባሪያ ነኝ፤ ባሕ​ሩ​ንና የብ​ሱን የፈ​ጠ​ረ​ውን የሰ​ማ​ይን አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን አመ​ል​ካ​ለሁ” አላ​ቸው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዮናስ 1:9
29 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

አንተ ብቻህን ጌታ ነህ፥ ሰማይንና የሰማያት ሰማይን ሠራዊታቸውንም ሁሉ፥ ምድርንና በእርሷ ያሉትን ሁሉ፥ ባሕሮቹንና በእነርሱ ውስጥ ያለውን ሁሉ፥ ፈጠርህ፥ ለሁሉም ሕይወትን ሰጠሃቸው፤ የሰማይ ሠራዊት ለአንተ ይሰግዳሉ።


የሰማይን አምላክ አመስግኑ፥ ፍቅሩ ለዘለዓለም ነውና።


እነዚህን ቃላት በሰማሁ ጊዜ ተቀምጬ አለቀስሁ። ለብዙ ቀኖች አዘንሁ፤ በሰማይ አምላክ ፊት እጾምና እጸልይ ነበር፥


የፋርስ ንጉሥ ቂሮስ እንዲህ ይላል፦ “የሰማያት አምላክ ጌታ የምድርን መንግሥታት ሁሉ ሰጥቶኛል፥ በይሁዳም ባለችው በኢየሩሳሌም ቤት እንድሠራለት አዝዞኛል፤


ስለዚህም ከሰማርያ ተማርኮ የተወሰደ አንድ እስራኤላዊ ካህን ተመልሶ በመሄድ በቤትኤል ተቀመጠ፤ በዚያም ሕዝቡ እግዚአብሔርን እንዴት ማምለክ እንደሚገባው አስተማረው።


እነርሱም በዚያ ሰፍረው መኖር እንደ ጀመሩ እግዚአብሔርን አላመለኩትም ነበር። ስለዚህም እግዚአብሔር አንበሶችን በመላክ ከእነርሱ ጥቂቶቹን ሰባብረው እንዲገድሉ አደረገ፤


አንድ የሸሸ ሰውም መጣ፥ ለዕብራዊው ለአብራምም ነገረው፥ እርሱም የኤስኮል ወንድምና የአውናን ወንድም በሆነ በአሞራዊ መምሬ የባሉጥ ዛፎች አጠገብ ይኖር ነበር፥ እነዚያም ከአብራም ጋር ቃል ኪዳን ገብተው ነበር።


ከስቃያቸውና ከቁስላቸውም የተነሣ የሰማይን አምላክ ተሳደቡ፤ ከሥራቸውም ንስሓ አልገቡም።


በዚያም ሰዓት ታላቅ የምድር መናወጥ ሆነ፤ ከከተማይቱም ዐሥረኛው እጅ ወደቀ፤ በመናወጥም ሰባት ሺህ ሰዎች ተገደሉ፤ የቀሩትንም ፍርሃት ያዛቸው፤ ለሰማዩም አምላክ ክብር ሰጡ።


በስምንተኛው ቀን የተገረዝሁ፥ ከእስራኤል ትውልድ፥ ከብንያም ወገን፥ ከዕብራውያን ዕብራዊ ነኝ፤ ስለ ሕግ ብትጠይቁ፥ ፈሪሳዊ ነበርሁ፤


የእርሱ የምሆንና ደግሞ የማመልከው የእግዚአብሔር መልአክ በዚች ሌሊት በአጠገቤ ቆሞ ነበርና፤ እርሱም


እንዲህም አሉ “እናንተ ሰዎች! ይህን ስለምን ታደርጋላችሁ? እኛ ደግሞ እንደ እናንተ የምንሰማ ሰዎች ነን፤ ከዚህም ከንቱ ነገር ሰማይንና ምድርን ባሕርንም በእርነርሱም ያለውን ሁሉ ወደ ፈጠረ ወደ ሕያው እግዚአብሔር ትመለሱ ዘንድ ወንጌልን እንሰብካለን።


ከዚያም በኋላ የእስራኤል ልጆች ተመልሰው አምላካቸውን ጌታንና ንጉሣቸውን ዳዊትን ይፈልጋሉ፤ በኋለኛውም ዘመን ፈርተው ወደ ጌታና ወደ መልካምነቱ ይመጣሉ።


ሰይጣንም ለጌታ እንዲህ ብሎ መለሰለት፦ “በውኑ ኢዮብ እግዚአብሔርን የሚፈራ በከንቱ ነውን?


ንጉሡም፦ “ምን ትፈልጋልህ?” አለኝ። እኔም ወደ ሰማይ አምላክ ጸለይሁ።


የመለሱልን መልስ ይህ ነው፦ ‘እኛ የሰማያትና የምድር አምላክ አገልጋዮች ነን፥ ከብዙም ዘመን ጀምሮ ተሠርቶ የነበረ፥ ታላቅ የእሥራኤል ንጉሥ ሠርቶ የፈጸመውን ቤት እንሠራለን።


የቤት አገልጋዮቿን ጠራች፤ እንዲህም አለቻቸው፤ “አያችሁ፤ ለካስ ይህ ዕብራዊ የመጣው መሣለቂያ ሊያደርገን ኖሮአል! እዚህ ድረስ ሰተት ብሎ ገብቶ ካልተኛሁሽ አለኝ፤ እኔም ጩኸቴን ለቀቅሁት፤


የግብጽም ንጉሥ የዕብራውያንን አዋላጆች አንዲቱ ሺፍራ ሁለተኛይቱም ፑአ የሚባሉትን እንዲህ አላቸው፦


በሁለተኛውም ቀን ወጣ፥ ሁለት ዕብራውያን ሰዎች ሲጣሉ አየ፥ በዳዩንም፦ “ለምን ባልንጀራህን ትመታዋለህ?” አለው።


እግዚአብሔርም የብሱን “ምድር” ብሎ ጠራው፥ በአንድ ስፍራ የተሰበሰበውንም ውሃ “ባሕር” አለው፥ እግዚእብሔርም ያ መልካም እንደሆነ አየ።


ከአባቴ ቤት ከተወለድሁባት ምድርም ያወጣኝ፦ ‘ይህችንም ምድር ለዘርህ እሰጥሃለሁ’ ብሎ የነገረኝና የማለልኝ የሰማይ አምላክ እግዚአብሔር፥ እርሱ መልአኩን በፊትህ ይሰድዳል፥ ከዚያም ለልጄ ሚስትን ትወስዳለህ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች