Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ዮሐንስ 9:35 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

35 ኢየሱስም ወደ ውጭ እንዳወጡት ሰማ፤ ሲያገኘውም “አንተ በሰው ልጅ ታምናለህን?” አለው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

35 ኢየሱስም ሰውየውን እንዳባረሩት ሰማ፤ ባገኘውም ጊዜ፣ “በሰው ልጅ ታምናለህን?” አለው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

35 ሰውየውን ከምኲራብ እንዳስወጡት ኢየሱስ ሰማ፤ ባገኘውም ጊዜ “በሰው ልጅ ታምናለህን?” አለው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

35 ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም ወደ ውጭ እን​ዳ​ወ​ጡት ሰማ፤ አገ​ኘ​ው​ምና፥ “አንተ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ልጅ ታም​ና​ለ​ህን?” አለው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

35 ኢየሱስም ወደ ውጭ እንዳወጡት ሰማ ያገኘውም፦ “አንተ በእግዚአብሔር ልጅ ታምናለህን?” አለው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዮሐንስ 9:35
32 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ነገር ግን ኢየሱስ መሢሕ፥ የእግዚአብሔር ልጅ እንደሆነ ታምኑ ዘንድ፥ አምናችሁም በስሙ ሕይወት ይሆንላችሁ ዘንድ ይህ ተጽፎአል።


በእግዚአብሔር ልጅ ስም ለምታምኑ፥ የዘለዓለም ሕይወት እንዳላችሁ እንድታውቁ ይህን ጽፌላችኋለሁ።


የእግዚአብሔር ልጅ ነኝ ስላልሁ አብ የቀደሰውንና ወደ ዓለም የላከውን እናንተ ‘ትሳደባለህ፤’ ትሉታላችሁን?


የእግዚአብሔር ልጅ እንደመጣ፥ እውነት የሆነውን እንድናውቅ ማስተዋልን እንደ ሰጠን እናውቃለን፤ እውነት በሆነው በእርሱ እንኖራለን፥ እርሱም ልጁ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው። እርሱ እውነተኛ አምላክና የዘለዓለም ሕይወት ነው።


በእግዚአብሔር ልጅ የሚያምን በራሱ ምስክር አለው፤ እግዚአብሔርን የማያምን ግን እግዚአብሔር ስለ ልጁ የመሰከረውን ምስክርነት ስላላመነ ሐሰተኛ አድርጎታል።


ኢየሱስ የእግዚአብሔር ልጅ እንደሆነ ከሚያምን በስተቀር ዓለምን የሚያሸንፍ ማን ነው?


ኢየሱስ የእግዚአብሔር ልጅ እንደሆነ የሚመሰክር ሁሉ፥ እግዚአብሔር በእርሱ ይኖራል እርሱም በእግዚአብሔር ይኖራል።


ስለዚህ ኢሳይያስም በድፍረት “ላልፈለጉኝ ተገኘሁ፤ ላልጠየቁኝም ተገለጥሁ” አለ።


ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በቅድስና መንፈስ ከሙታን በመነሣት በኃይል የእግዚአብሔር ልጅ ሆኖ መገለጡ ነው፤


ወዲያውም ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ እርሱ የእግዚአብሔር ልጅ እንደሆነ በምኵራቦቹ ሰበከ።


በመንገድም ሲሄዱ ወደ ውሃ ደረሱ፤ ጃንደረባውም “እነሆ ውሃ፤ እንዳልጠመቅ የሚከለክለኝ ምንድነው?” አለው።


ቶማስም “ጌታዬና አምላኬ!” ብሎ መለሰለት።


እርሷም “አዎን ጌታ ሆይ፤ አንተ ወደ ዓለም የሚመጣው ክርስቶስ የእግዚአብሔር ልጅ እንደሆንህ እኔ አምናለሁ” አለችው።


እኛስ አንተ የሕያው የእግዚአብሔር ቅዱስ እንደሆንህ አምነናል፤ አውቀናልም፤” ብሎ መለሰለት።


ከዚህ በኋላ ኢየሱስ በቤተ መቅደስ አገኘውና “እነሆ፥ ድነሃል፤ ከዚህ የሚብስ እንዳይደርስብህ ወደ ፊት ኃጢአት አትሥራ፤” አለው።


በልጁ የሚያምን የዘለዓለም ሕይወት አለው፤ ለልጁ የማይታዘዝ ግን የእግዚአብሔር ቁጣ በእርሱ ላይ ይኖራል እንጂ ሕይወትን አያይም።


እኔም አይቻለሁ፥ እርሱም የእግዚአብሔር ልጅ እንደሆነ መስክሬአለሁ።”


እግዚአብሔርን ያየው ከቶ ማንም የለም፤ በአባቱ እቅፍ ያለ አንድ ልጁ እርሱ ገለጠው።


የእግዚአብሔር ልጅ፥ የኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌል መጀመሪያ፥


ስምዖን ጴጥሮስም “አንተ ክርስቶስ የሕያው እግዚአብሔር ልጅ ነህ” ብሎ መለሰ።


በጀልባዋ የነበሩትም “በእውነት የእግዚአብሔር ልጅ ነህ” ብለው ሰገዱለት።


አባቴና እናቴ ትተውኛልና፥ ጌታ ግን ተቀበለኝ።


ተግሣጹን ተቀበሉ ጌታ እንዳይቈጣ እናንተም በመንገድ እንዳትጠፉ፥ ቁጣው ፈጥና ትነድዳለችና። በእርሱ የታመኑ ሁሉ የተመሰገኑ ናቸው።


ትእዛዙን እናገራለሁ፥ ጌታ አለኝ፦ “አንተ ልጄ ነህ፥ እኔ ዛሬ ወለድሁህ።”


ፈታኙ መጥቶ “የእግዚአብሔር ልጅ ከሆንህ፥ እነዚህ ድንጋዮች እንጀራ እንዲሆኑ እዘዝ” አለው።


ወላጆቹ አይሁድን ስለ ፈሩ ይህንን አሉ፤ “እርሱ ክርስቶስ ነው፤” ብሎ የሚመሰክር ቢኖር ከምኵራብ እንዲያወጡት አይሁድ ከዚህ በፊት ተስማምተው ነበርና።


መልሰው “አንተ ሙሉ በሙሉ በኃጢአት ተወልድህ፤ እኛን ታስተምረናለህን?” አሉት። ወደ ውጭም አወጡት።


ስለዚህ እኔ ከመጣሁ፥ ስለ እኛ የተናገረውን ክፉ ቃል፥ የሠራውን ሥራ አሳስበዋለሁ፤ ይህም ሳይበቃው እርሱ ራሱ ወንድሞችን አይቀበልም፤ ሊቀበሉአቸው የሚፈልጉትን ይከለክላቸዋል፥ ከቤተ ክርስቲያንም ያስወጣቸዋል።


ፊልጶስም “በፍጹም ልብህ ብታምን፥ ተፈቅዶአል፤” አለው። መልሶም “ኢየሱስ ክርስቶስ የእግዚአብሔር ልጅ እንደሆነ አምናለሁ፤” አለ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች