ዮሐንስ 9:22 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)22 ወላጆቹ አይሁድን ስለ ፈሩ ይህንን አሉ፤ “እርሱ ክርስቶስ ነው፤” ብሎ የሚመሰክር ቢኖር ከምኵራብ እንዲያወጡት አይሁድ ከዚህ በፊት ተስማምተው ነበርና። ምዕራፉን ተመልከትአዲሱ መደበኛ ትርጒም22 ኢየሱስን፣ ክርስቶስ ነው ብሎ የመሰከረ ሁሉ ከምኵራብ እንዲባረር አይሁድ አስቀድመው ወስነው ስለ ነበር፣ ወላጆቹ ይህን ያሉት አይሁድን ፈርተው ነው። ምዕራፉን ተመልከትአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም22 ወላጆቹ ይህን ያሉት ኢየሱስን “መሲሕ ነው” የሚል ሰው ቢኖር የአይሁድ ባለሥልጣኖች ከምኲራብ ሊያስወጡት ተስማምተው ስለ ነበረ እነርሱን በመፍራት ነበር። ምዕራፉን ተመልከትየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)22 ወላጆቹ አይሁድን ስለ ፈሩ ይህን አሉ፥ “እርሱ ክርስቶስ ነው ብሎ በእርሱ የሚያምን ቢኖር ከምኵራብ ይውጣ” ብለው አይሁድ ተስማምተው ነበርና። ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)22 ወላጆቹ አይሁድን ስለ ፈሩ ይህን አሉ፤ እርሱ ክርስቶስ ነው ብሎ የሚመሰክር ቢኖር ክምኵራብ እንዲያወጡት አይሁድ ከዚህ በፊት ተስማምተው ነበርና። ምዕራፉን ተመልከት |