Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ዮሐንስ 7:45 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

45 ዘቦቹም ወደ ካህናት አለቆችና ወደ ፈሪሳውያን መጡ፤ እነርሱም “ለምንድነው ያላመጣችሁት?” አሉአቸው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

45 በመጨረሻም የቤተ መቅደስ ጠባቂዎቹ፣ ወደ ካህናት አለቆችና ወደ ፈሪሳውያን ተመልሰው ሄዱ፤ እነርሱም ጠባቂዎቹን፣ “ለምን አላመጣችሁትም?” አሏቸው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

45 ከዚህ በኋላ ዘብ ጠባቂዎቹ ወደ ካህናት አለቆችና ወደ ፈሪሳውያን ተመልሰው ሄዱ፤ እነርሱም “ስለምን አላመጣችሁትም?” አሉአቸው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

45 ሎሌ​ዎ​ቹም ወደ ካህ​ናት አለ​ቆ​ችና ወደ ፈሪ​ሳ​ው​ያን ተመ​ለሱ፤ እነ​ር​ሱም፥ “ያላ​መ​ጣ​ች​ሁት ለም​ን​ድን ነው?” አሉ​አ​ቸው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

45 ሌሎቹም ወደ ካህናት አለቆችና ወደ ፈሪሳውያን መጡ፤ እነዚያም፦ “ያላመጣችሁት ስለ ምን ነው?” አሉአቸው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዮሐንስ 7:45
6 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ፈሪሳውያን ሕዝቡ ስለ እርሱ እንደዚህ ሲያንጐራጉሩ ሰሙ፤ የካህናት አለቆችና ፈሪሳውያንም ሊይዙት ዘቦችን ላኩ።


ጴጥሮስም እስከ ሊቀ ካህኑ ግቢ ድረስ ሩቅ ሆኖ ተከተለው፤ የነገሩንም ፍጻሜ ለማየት ወደ ውስጥ ገብቶ ከሎሌዎቹ ጋር ተቀመጠ።


ወላጆቹ አይሁድን ስለ ፈሩ ይህንን አሉ፤ “እርሱ ክርስቶስ ነው፤” ብሎ የሚመሰክር ቢኖር ከምኵራብ እንዲያወጡት አይሁድ ከዚህ በፊት ተስማምተው ነበርና።


ከእነርሱ አንዳንዶቹ ግን ወደ ፈሪሳውያን ሄደው ኢየሱስ ያደረገውን ነገሩአቸው።


የካህናት አለቆችና ፈሪሳውያንም ሸንጎ ሰብስበው እንዲህ አሉ፥ “ምን እናድርግ? ይህ ሰው ብዙ ምልክቶችን ያደርጋልና።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች