Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ዮሐንስ 6:61 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

61 ኢየሱስ ግን ደቀመዛሙርቱ በዚህ ምክንያት እንዳንጐራጐሩ በልቡ አውቆ እንዲህ አላቸው “ይህ ያስናክላችኋልን?

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

61 ደቀ መዛሙርቱም በዚህ ነገር ማጕረምረማቸውን ኢየሱስ በገዛ ራሱ ተረድቶ፣ እንዲህ አላቸው፤ “ይህ ዕንቅፋት ይሆንባችኋልን?

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

61 ኢየሱስም ደቀ መዛሙርቱ ስለዚህ ነገር እንዳጒረመረሙ በመንፈሱ ዐውቆ እንዲህ አላቸው፦ “ይህ ነገር ያሰናክላችኋልን?

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

61 ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም ደቀ መዛ​ሙ​ርቱ ስለ​ዚህ ነገር እንደ አን​ጐ​ራ​ጐሩ በልቡ ዐወ​ቀ​ባ​ቸ​ውና እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “ይህ ያሰ​ና​ክ​ላ​ች​ኋ​ልን?

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

61 ማን ሊሰማው ይችላል? አሉ። ኢየሱስ ግን ደቀ መዛሙርቱ ስለዚህ እንዳንጐራጐሩ በልቡ አውቆ አላቸው፦ ይህ ያስናክላችኋላን?

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዮሐንስ 6:61
8 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

በእኔ የማይሰናከል ሁሉ የተባረከ ነው።”


ነገር ግን እንቅፋት እንዳንሆንባቸው ወደ ባሕር ሂድና መንጠቆ ጣል፥ በመጀመሪያ የሚወጣውን ዓሣ ውሰድ፥ አፉን ስትከፍት እስታቴር ታገኛለህ፤ ያን ወስደህ የእኔንና የአንተን ክፈል።”


ኢየሱስም ሊጠይቁት እንደ ወደዱ አውቆ እንዲህ አላቸው “‘ከጥቂት ጊዜ በኋላ አታዩኝም፤ ከጥቂት ጊዜ በኋላ ደግሞ ታዩኛላችሁ፤’ ስላልሁ፥ እርስ በርሳችሁ ትመራመራላችሁን?


ለሦስተኛ ጊዜም “የዮና ልጅ ስምዖን ሆይ! ትወደኛለህን?” አለው። ለሦስተኛ ጊዜ “ትወደኛለህን?” ስላለው ጴጥሮስ አዘነና “ጌታ ሆይ! አንተ ሁሉን ታውቃለህ፤ እንደምወድህ አንተ ታውቃለህ” አለው። ኢየሱስም “በጎቼን አሰማራ።


ነገር ግን ከእናንተ የማያምኑ አሉ።” ኢየሱስ የማያምኑት እነማን እንደ ሆኑ፥ አሳልፎ የሚሰጠውም ማን እንደሆነ ከመጀመሪያው ያውቅ ነበርና።


በፊቱም የሚሰወር ምንም ፍጥረት የለም፤ እኛ መልስ መስጠት በሚገባን ከእርሱ ፊት ሁሉ ነገር ግልጥና ዕርቃኑን ሆኖ የሚታይ ነው።


ልጆችዋንም በሞት እገድላቸዋለሁ፤ አብያተ ክርስቲያናትም ሁሉ፥ ኩላሊትንና ልብን የምመረምር እኔ እንደሆንሁ ያውቃሉ፤ ለእያንዳንዳችሁም እንደ ሥራችሁ እሰጣችኋለሁ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች