Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ዮሐንስ 6:29 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

29 ኢየሱስ መልሶ “የእግዚአብሔር ሥራ ይህ ነው፤ ይህም እርሱ በላከው እንድታምኑ ነው፤” አላቸው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

29 ኢየሱስም፣ “እርሱ በላከው ታምኑ ዘንድ፣ ይህ የእግዚአብሔር ሥራ ነው” ሲል መለሰላቸው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

29 ኢየሱስም “የእግዚአብሔር ሥራማ እግዚአብሔር በላከው ማመን ነው” ሲል መለሰላቸው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

29 ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም መልሶ፥ “ይህ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሥራ እርሱ በላ​ከው ታምኑ ዘንድ ነው፤” አላ​ቸው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

29 ኢየሱስ መልሶ፦ ይህ የእግዚአብሔር ሥራ እርሱ በላከው እንድታምኑ ነው አላቸው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዮሐንስ 6:29
21 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ትእዛዚቱም ይህች ናት፥ በልጁ በኢየሱስ ክርስቶስ ሥም እንድናምንና፥ እርሱም እንዳዘዘን እርስ በርሳችን እንድንዋደድ ነው።


እነርሱም “በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ እመን፤ አንተና ቤተ ሰዎችህ ትድናላችሁ፤” አሉት።


ፍጹም ሆኖ ከተገኘም በኋላ ለሚታዘዙት ሁሉ ለዘለዓለም መዳን ምክንያት ሆነላቸው።


በልጁ የሚያምን የዘለዓለም ሕይወት አለው፤ ለልጁ የማይታዘዝ ግን የእግዚአብሔር ቁጣ በእርሱ ላይ ይኖራል እንጂ ሕይወትን አያይም።


ኢየሱስ መሢሕ መሆኑን የሚያምን ሁሉ ከእግዚአብሔር ተወልዶአል፥ ወላጁንም የሚወድ ሁሉ ከእርሱ የተወለደውን ደግሞ ይወዳል።


ያመነና የተጠመቀ ይድናል፤ ያላመነ ግን ይፈረድበታል።


እናንተ መጻሕፍትን ትመረምራላችሁ፤ በእነርሱም የዘለዓለም ሕይወት እንዳላችሁ ታስባላችሁና፤ እነርሱም ስለ እኔ የሚመሰክሩ ናቸው፤


ተግሣጹን ተቀበሉ ጌታ እንዳይቈጣ እናንተም በመንገድ እንዳትጠፉ፥ ቁጣው ፈጥና ትነድዳለችና። በእርሱ የታመኑ ሁሉ የተመሰገኑ ናቸው።


እርሱም ገና እየተናገረ ሳለ እነሆ ብሩህ ደመና ጋረዳቸው፤ እነሆ ከደመናው ውስጥ “በእርሱ ደስ የሚለኝ የተወደደው ልጄ ይህ ነው፤ እርሱን ስሙት” የሚል ድምፅ መጣ።


እንግዲህ “የእግዚአብሔርን ሥራ ለመሥራት ምን እናድርግ?” አሉት።


ፈቃዴን ለማድረግ ሳይሆን የላከኝን ፈቃድ ለማድረግ ከሰማይ ወርጃለሁና።


ሕያው አብ እንደ ላከኝ፥ እኔም በአብ የተነሣ ሕያው እንደምሆን፥ እንዲሁ የሚመገበኝ ደግሞ በእኔ ሕያው ይሆናል።


በእግዚአብሔር በአባታችን ፊት የእምነታችሁን ሥራ፥ የፍቅራችሁን ድካም፥ በጌታችንም በኢየሱስ ክርስቶስ ያላችሁን የተስፋችሁንም መጽናት እናስታውሳለን።


ስለዚህ እምነት ከሥራው ጋር አብሮ እንደ ነበርና እምነትም በሥራ ፍጹም እንደሆነ ታያለህን?


ድል ለነሣውና እስከ መጨረሻም ሥራዬን ለጠበቀው እኔ ደግሞ ከአባቴ እንደ ተቀበልሁ በአሕዛብ ላይ ሥልጣንን እሰጠዋለሁ፤ በብረትም በትር ይገዛቸዋል፤ እንደ ሸክላ ዕቃም ይቀጠቀጣሉ፤


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች