Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ዮሐንስ 6:19 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

19 ሃያ አምስት ወይም ሠላሳ ምዕራፍ ከቀዘፉ በኋላም፥ ኢየሱስ በባሕር ላይ እየተራመደ ወደ ታንኳይቱ ሲቀርብ አይተው ፈሩ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

19 ዐምስት ወይም ስድስት ኪሎ ሜትር ያህል እንደ ቀዘፉ፣ ኢየሱስ በውሃ ላይ እየተራመደ ወደ ጀልባዋ ሲመጣ አይተው ፈሩ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

19 ደቀ መዛሙርቱ አምስት ወይም ስድስት ኪሎ ሜትር ያኽል እየቀዘፉ ከተጓዙ በኋላ ኢየሱስ በባሕሩ ላይ እየተራመደ ወደ ጀልባዋ ሲቀርብ አይተው ፈሩ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

19 ሃያ አም​ስት ወይም ሠላሳ ምዕ​ራፍ ያህል ከሄዱ በኋላ ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስን በባ​ሕር ላይ ሲሄድ አዩት፤ ወደ ታን​ኳዉ በቀ​ረበ ጊዜም ፈሩ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

19 ሀያ አምስት ወይም ሠላሳ ምዕራፍ ከቀዘፉ በኋላም፥ ኢየሱስ በባሕር ላይ እየሄደ ወደ ታንኳይቱ ሲቀርብ አይተው ፈሩ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዮሐንስ 6:19
16 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

“ወላጆች እንደሌላቸው ልጆች አልተዋችሁም፤ ወደ እናንተ እመጣለሁ።


ከብዙ ውኆች ድምፅ ከባሕርም ታላቅ ሞገድ ይልቅ ጌታ በከፍታው ድንቅ ነው።


ሰማያትን ብቻውን ይዘረጋል፥ በባሕሩም ማዕበል ላይ ይረግጣል።


ሰዎቹ ወደ የብሱ ሊመለሱ አጥብቀው ቀዘፉ፥ ነገር ግን አልቻሉም፥ ባሕሩ በማዕበሉ ይናወጥባቸው ነበርና።


ቀዛፊዎችሽ ወደ ታላቅ ውኆች አመጡሽ፤ የምሥራቅ ነፋስ በባሕር ልብ ሰበረሽ።


ጌታ የጥፋት ውኃን ሰብስቦአል፥ ጌታ ለዘለዓለም ንጉሥ ሆኖ ይቀመጣል።


ከተማይቱም አራት ማዕዘን ነበራት፤ ርዝመትዋም እንደ ስፋትዋ ልክ ነበረ። ከተማይቱንም በዘንግ ለካት፤ ሁለት ሺህ አራት መቶ ኪሎ ሜትር ሆነች፤ ርዝመትዋና ስፋትዋ ከፍታዋም ትክክል ነው።


የወይኑም መጥመቂያ ከከተማ ውጭ ተረገጠ፤ እስከ ፈረሶች ልጓም የሚደርስና እስከ አንድ ሺህ ስድስት መቶ ምዕራፍ ድረስ የሚርቅ ደም ከመጥመቂያው ወጣ።


ቢታንያም ዐሥራ አምስት ምዕራፍ ያህል ለኢየሩሳሌም ቅርብ ነበረች።


እነሆም፥ ከእነርሱ ሁለቱ በዚያ ቀን ከኢየሩሳሌም ዐሥራ ሁለት ኪሎ ሜትር ያህል ወደሚርቅ ኤማሁስ ወደሚባል መንደር ይሄዱ ነበር፤


ልጁም በመምጣት ላይ ሳለ ጋኔኑ ጣለውና አንፈራገጠው፤ ኢየሱስ ግን ርኩሱን መንፈስ ገሥጾ ብላቴናውን ፈወሰው፤ ልጁንም ለአባቱ መልሶ ሰጠው።


ብርቱ ነፋስም ስለ ነፈሰ ባሕሩ ተናወጠ።


እርሱ ግን “እኔ ነኝ፤ አትፍሩ፤” አላቸው።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች