Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ዮሐንስ 5:34 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

34 እኔ ግን የሰው ምስክር የሚያስፈልገኝ አይደለሁም፤ እናንተ እንድትድኑ ይህን እላለሁ እንጂ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

34 እኔ የሰው ምስክርነት የምቀበል አይደለሁም፤ ይህን የምናገረው ግን እናንተ እንድትድኑ ነው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

34 ይህንንም ማለቴ እንድትድኑ ነው እንጂ እኔ የሰው ምስክርነት ስላስፈለገኝ አይደለም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

34 እኔ ግን የሰ​ውን ምስ​ክ​ር​ነት የምሻ አይ​ደ​ለ​ሁም፤ ነገር ግን እና​ንተ ትድኑ ዘንድ ይህን እላ​ለሁ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

34 እኔ ግን ከሰው ምስክር አልቀበልም፥ እናንተ እንድትድኑ ይህን እላለሁ እንጂ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዮሐንስ 5:34
16 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

የሰውን ምስክርነት የምንቀበል ከሆነ የእግዚአብሔር ምስክርነት ይበልጣል፤ እግዚአብሔር ስለ ልጁ የመሰከረው ምስክርነት ይህ ነውና።


ነገር ግን ኢየሱስ መሢሕ፥ የእግዚአብሔር ልጅ እንደሆነ ታምኑ ዘንድ፥ አምናችሁም በስሙ ሕይወት ይሆንላችሁ ዘንድ ይህ ተጽፎአል።


ለራስህና ለምታስተምረው ትምህርት ተጠንቀቅ፤ በእነዚህም ነገሮች ጽና፤ ይህን ብታደርግ፥ ራስህንና የሚሰሙህን ታድናለህ።


ደካሞችን መጥቀም እንድችል ለደካሞች እንደ ደካማ ሆንኩ፤ በሁሉ መንገድ አንዳንዶችን ማዳን እንድችል፥ ከሁሉ ጋር በሁሉ ነገር እንደ እነርሱ ሆንሁ።


ወንድሞች ሆይ! የልቤ መልካም ምኞትና እግዚአብሔርንም የምለምነው እስራኤላውያን እንዲድኑ ነው።


አንዳንዶች ባያምኑስ? የእነሱ አለማመን የእግዚአብሔርን ታማኝነት ዋጋ የሌለው ያደርገዋልን?


ኢየሱስም እንዲህ ሲል መለሰ፤ “እኔ እራሴን ባከብር ክብሬ ከንቱ ነው፤ የሚያከብረኝ እናንተ አምላካችን የምትሉት አባቴ ነው፤


የሰው ክብር አያስፈልገኝም፤


በስሙም ንስሐና የኃጢአት ስርየት ከኢየሩሳሌም ጀምሮ በአሕዛብ ሁሉ እንደሚሰበክ፤


ክፉውን በመልካም አሸንፍ እንጂ በክፉ አትሸነፍ።


ስለ እስራኤል ግን “ወደማይታዘዝና ወደሚቃወም ሕዝብ ቀኑን ሙሉ እጆቼን ዘረጋሁ” ይላል።


የሰው ልጅ የጠፋውን ሊፈልግና ሊያድን መጥቶአለና፤” አለው።


ኢየሩሳሌም! ኢየሩሳሌም! ነቢያትን የምትገድል፥ ወደ እርሷ የተላኩትንም የምትወግር፥ ዶሮ ጫጩቶችዋን በክንፎችዋ በታች እንደምትሰበስብ ልጆችሽን ለመሰብሰብ ስንት ጊዜ ፈለግሁ፤ እናንተ ግን አልፈለጋችሁም።


ስለ እኔ የሚመሰክር ሌላ ነው፤ እርሱም ስለ እኔ የሚመሰክረው ምስክር እውነት እንደሆነ አውቃለሁ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች