Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ዮሐንስ 4:7 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

7 አንዲት የሰማርያ ሴት ውሃ ልትቀዳ መጣች። ኢየሱስም “ውሃ አጠጪኝ” አላት፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

7 አንዲት ሳምራዊት ሴት ውሃ ለመቅዳት ስትመጣ ኢየሱስ፣ “እባክሽ የምጠጣው ስጪኝ” አላት፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

7 በዚያን ጊዜ አንዲት የሰማርያ አገር ሴት ውሃ ልትቀዳ ወደ ጒድጓዱ መጣች፤ ኢየሱስም “ውሃ አጠጪኝ!” አላት።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

7 እነሆ፥ ከሰ​ማ​ርያ አን​ዲት ሴት ውኃ ልት​ቀዳ መጣች፤ ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም፥ “ውኃ አጠ​ጪኝ” አላት።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

7 ከሰማርያ አንዲት ሴት ውኃ ልትቀዳ መጣች። ኢየሱስም፦ ውኃ አጠጪኝ አላት፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዮሐንስ 4:7
9 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ሎሌውም ሊያናግራት ሮጠና፦ “ከእንስራሽ ጥቂት ውኃ ታጠጪኝ ዘንድ እለምንሻለሁ” አላት።


እነሆ፥ እኔ በውኃው ምንጭ ላይ ቆሜአለሁ፥’ ውኃ ልትቀዳ ለምትመጣውም ቆንጆ፦ ‘ጥቂት ውኃ ከእንስራሽ አጠጪኝ’ ስላት፥


ስለዚህ ኤልያስ ወደ ሰራጵታ ሄደ፤ ወደ ከተማይቱም ቅጽር በር በደረሰ ጊዜ አንዲት ባሏ የሞተባት ሴት እንጨት ስትለቅም አይቶ “እባክሽ የምጠጣው ውሃ አምጪልኝ” አላት።


ማንም ከእነዚህ ከታናናሾቹ ለአንዱ ቀዝቃዛ ውሃ በደቀ መዝሙር ስም ብቻ የሚያጠጣ፥ እውነት እላችኋለሁ፥ ዋጋውን አያጣም።”


ከዚህ በኋላ ኢየሱስ ከወዲሁ ሁሉ ነገር እንደ ተፈጸመ አውቆ የመጽሐፉም ቃል ይፈጸም ዘንድ “ተጠማሁ” አለ።


ኢየሱስ መልሶ “የእግዚአብሔርን ስጦታና ‘ወሃ አጠጪኝ’ የሚልሽ ማን መሆኑን ብታውቂ ኖሮ፥ አንቺ በለመንሽው ነበር፤ የሕይወትም ውሃ በሰጠሽ ነበር፤” አላት።


በዚያም የያዕቆብ ጉድጓድ ነበረ። ኢየሱስም መንገድ ከመሄድ ደክሞ በጉድጓድ አጠገብ ተቀመጠ፤ ጊዜውም ስድስት ሰዓት ያህል ነበረ።


ደቀመዛሙርቱ ምግብ ሊገዙ ወደ ከተማ ሄደው ነበርና።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች