Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ዮሐንስ 4:20 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

20 አባቶቻችን በዚህ ተራራ ሰገዱ፤ እናንተ ‘ሰው ሊሰግድበት የሚገባው ስፍራ በኢየሩሳሌም ነው፤’ ትላላችሁ፤” አለችው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

20 አባቶቻችን በዚህ ተራራ ላይ ሰገዱ፤ እናንተ አይሁድ ግን ሰው መስገድ ያለበት በኢየሩሳሌም ነው ትላላችሁ” አለችው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

20 አባቶቻችን በዚህ ተራራ ላይ ሰገዱ፤ እናንተ ግን ‘ሰዎች ሊሰግዱ የሚገባቸው በኢየሩሳሌም ነው’ ትላላችሁ።”

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

20 አባ​ቶ​ቻ​ችን በዚህ ተራራ ሰገዱ፤ እና​ንተ ግን ይሰ​ግ​ዱ​በት ዘንድ የሚ​ገ​ባው ስፍራ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ነው ትላ​ላ​ችሁ።”

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

20 አባቶቻችን በዚህ ተራራ ሰገዱ፤ እናንተ፦ ሰው ሊሰግድበት የሚገባው ስፍራ በኢየሩሳሌም ነው ትላላችሁ አለችው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዮሐንስ 4:20
20 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

“በፊቴ ያቀረብከውን ጸሎትና ልመና ሰምቼአለሁ፤ እርሱም ለዘለዓለም ለስሜ መጠሪያ እንዲሆን የሠራኸውን ቤተ መቅደስ ቀድሼዋለሁ፤ ዘወትርም እጠብቀዋለሁ።


ዳዊትም በዚያ ለጌታ መሠዊያ ሠራ፥ የሚቃጠለውን መሥዋዕትና የአንድነቱን መሥዋዕት አቀረበ፥ ጌታንም ጠራ፤ ጌታም ከሰማይ የሚቃጠለው መሥዋዕት በሚቀርብበት መሠዊያ ላይ በእሳት መለሰለት።


ዳዊትም፦ “ይህ የጌታ የእግዚአብሔር ቤት ነው፥ ይህም ለእስራኤል የሚቃጠለው መሥዋዕት የሚቀርብበት መሠዊያ ነው” አለ።


ነገር ግን ስሜ በዚያ እንዲጠራባት ኢየሩሳሌምን መርጫለሁ፥ በሕዝቤም በእስራኤል ላይ እንዲሆን ዳዊትን መርጫለሁ።’


ጌታም ለሰሎሞን በሌሊት ተገልጦ እንዲህ አለው፦ “ጸሎትህን ሰምቻለሁ፥ ይህንም ስፍራ ለራሴ ለመሥዋዕት ቤት መርጫለሁ።


አሁንም ስሜ ለዘለዓለም በዚያ እንዲኖር ይህን ቤት መርጫለሁ ቀድሻለሁም፤ ዐይኖቼና ልቤም ዘወትር በዚያ ይሆናሉ።


ጌታ ጽዮንን መርጦአታልና፥ ማደሪያውም ትሆነው ዘንድ ወድዶአታልና፥ እንዲህ ብሎ፦


የይሁዳን ወገን ግን መረጠ፥ የወደደውን የጽዮንን ተራራ።


ጌታ እንዲህ ይላል፦ ሰማይ ዙፋኔ ነው፥ ምድርም የእግሬ መረገጫ ናት፤ የምትሠሩልኝ ቤት ምን ዓይነት ነው? የማርፍበትስ ስፍራ ምንድነው?


ነገር ግን ወደ ኢየሩሳሌም ሊሄድ ፊቱን አቅንቶ ስለ ነበረ የመንደሩ ሰዎች አልተቀበሉትም።


በእውኑ አንተ ይህን ጉድጓድ ከሰጠን ከአባታችን ከያዕቆብ ትበልጣለህን? እራሱም ልጆቹም ከብቶቹም ከዚህ ጠጥተዋል፤” አለችው።


“ልትወርሳት ወደምትሄድባት ምድር ጌታ አምላክህ በሚያስገባህ ጊዜ በረከቱን በገሪዛን ተራራ፥ መርገሙን ደግሞ በጌባል ተራራ ላይ ታሰማለህ።


“ዮርዳኖስን በተሻገራችሁ ጊዜ፥ ስምዖን፥ ሌዊ፥ ይሁዳ፥ ይሳኮር፥ ዮሴፍና ብንያም ሕዝቡን ለመባረክ በገሪዛን ተራራ ላይ ይቁሙ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች