Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ዮሐንስ 4:18 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

18 አምስት ባሎች ነበሩሽና፤ አሁን ከአንቺ ጋር ያለው ባልሽ አይደለም፤ በዚህስ እውነቱን ተናገርሽ፤” አላት።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

18 በርግጥ ዐምስት ባሎች ነበሩሽ፤ አሁን ከአንቺ ጋራ ያለውም ባልሽ ስላልሆነ፣ የተናገርሽው እውነት ነው።”

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

18 አምስት ባሎች ነበሩሽ፤ አሁንም ከአንቺ ጋር ያለው ሰው ባልሽ አይደለም፤ ስለዚህ እውነቱን ተናግረሻል።”

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

18 ቀድሞ አም​ስት ባሎች ነበ​ሩሽ፤ ዛሬ አብ​ሮሽ ያለው ግን ባልሽ አይ​ደ​ለም፤ ይህ​ንስ እው​ነት አልሽ።”

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

18 አምስት ባሎች ነበሩሽና፥ አሁን ከአንቺ ጋር ያለው ባልሽ አይደለም፤ በዚህስ እውነት ተናገርሽ አላት።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዮሐንስ 4:18
16 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

የእስራኤል ቤት ሆይ! በእውነት ሚስት ባልዋን እንደምታታልል እንዲሁ አታለላችሁኝ ይላል ጌታ።’”


እርሷም ባሏን ፈትታ ሌላ ብታገባ ታመነዝራለች” አላቸው።


ስለዚህ ባሏ በሕይወት እያለ ሌላ ባል ብታገባ አመንዝራ ትባላለች። ባሏ ቢሞት ግን ከሕጉ ነፃ ናት፥ ሌላ ባል ብታገባ አመንዝራ አይደለችም።


በባሏ ፋንታ ሌሎችን የምታስተናግድ አመንዝራ ሴት ሆነሻል።


ደግሞም የምዋቹ ስም ከወንድሞቹ መካከል ከአገሩም ደጅ እንዳይጠፋ፥ የምዋቹን ስም በርስቱ ላይ እንዳስነሣ የመሐሎንን ሚስት ሞዓባዊቱን ሩትን ሚስት ትሆነኝ ዘንድ ወሰድሁአት፥ እናንተም ዛሬ ምስክሮች ናችሁ” አላቸው።


“ሚስት በባልዋ ሥልጣን ሥር እያለች እርሱን ትታ ፈቀቅ በማለት ራስዋን በምታረክስ ጊዜ ያለው የቅንዓት ሕግ ይህ ነው፤


እነርሱም፦ “በጋለሞታ እንደሚደረግ በእኅታችን ሊደረግ ይገባልን?” አሉ።


የአገሩ ገዢ የሒዋዊው ሰው የኤሞር ልጅ ሴኬም አያት፥ ወሰዳትም ከእርሷም ጋር ተኛ፥ አስነወራትም።


እግዚአብሔርም ሌሊት በሕልም ወደ አቢሜሌክ መጣ፥ “እነሆ፥ አንተ ስለ ወሰድሃት ሴት ትሞታለህ፤ እርሷ ባለ ባል ናትና” አለው።


ጋብቻ በሁሉ ዘንድ ክቡር፥ መኝታውም ንጹሕ ይሁን፤ ሴሰኞችንና አመንዝሮችን ግን እግዚአብሔር ይፈርድባቸዋል።


ሴቲቱ መልሳ “ባል የለኝም፤” አለችው። ኢየሱስም “‘ባል የለኝም፤’ በማለትሽ መልካም ተናገርሽ፤


ሴቲቱ “ጌታ ሆይ! አንተ ነቢይ እንደሆንህ አያለሁ።


ስለዚህ አመንዝራ ሆይ፥ የጌታን ቃል ስሚ።


ኢየሱስም “ሂጂና ባልሽን ጠርተሽ ወደዚህ ነዪ፤” አላት።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች