ዮሐንስ 20:25 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)25 ሌሎቹም ደቀመዛሙርቱ “ጌታን አይተነዋል፤” አሉት። እርሱ ግን “የችንካሩን ምልክት በእጆቹ ላይ ካላየሁ፥ ጣቴንም በችንካሩ ምልክት ውስጥ ካላስገባሁ፥ እጄንም በጎኑ ቊስል ውስጥ ካላስገባሁ አላምንም፤” አላቸው። ምዕራፉን ተመልከትአዲሱ መደበኛ ትርጒም25 ሌሎች ደቀ መዛሙርትም፣ “ጌታን አየነው እኮ!” አሉት። እርሱ ግን፣ “በምስማር የተቸነከሩትን የእጆቹን ምልክቶች ካላየሁ፣ ምስማሮቹ በነበሩበት ቦታ ጣቴን ካላደረግሁ፣ በጐኑም እጄን ካላስገባሁ አላምንም” አለ። ምዕራፉን ተመልከትአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም25 ስለዚህ ሌሎች ደቀ መዛሙርት ቶማስን “ጌታን አየነው” አሉት። እርሱ ግን “በምስማር የተወጉትን እጆቹን ካላየሁና ጣቴን በምስማር በተወጋው ውስጥ ካላገባሁ፥ እጄንም በጐኑ ቊስል ካላገባሁ አላምንም” አላቸው። ምዕራፉን ተመልከትየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)25 ሌሎች ደቀ መዛሙርትም፥ “ጌታችንን አየነው” አሉት፤ እርሱ ግን፥ “የችንካሩን ምልክት በእጁ ካላየሁ፥ ጣቴንም ወደ ተቸነከረበት ካልጨመርሁ፥ እጄንም ወደ ጎኑ ካላገባሁ አላምንም” አላቸው። ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)25 ሌሎቹም ደቀ መዛሙርቱ፦ “ጌታን አይተነዋል” አሉት። እርሱ ግን፦ “የችንካሩን ምልክት በእዶቹ ካላየሁ ጣቴንም በችንካሩ ምልክት ካላገባሁ እጄንም በጎኑ ካላገባሁ አላምንም” አላቸው። ምዕራፉን ተመልከት |