Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ዮሐንስ 2:25 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

25 ስለ ሰው ማንም እንዲመሰክር አያስፈልገውም ነበር፤ በሰው ውስጥ ያለውን እራሱ ያውቅ ነበርና።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

25 በሰው ውስጥ ያለውን ያውቅ ስለ ነበር፣ ማንም ስለ ሰው እንዲመሰክርለት አላስፈለገውም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

25 እርሱ በሰው ልብ ያለውን ሁሉ ያውቅ ስለ ነበር ስለ ሰው ማንም እንዲነግረው አያስፈልገውም ነበር።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

25 የሰ​ው​ንም ግብ​ሩን ሊነ​ግ​ሩት አይ​ሻም፤ እርሱ በሰው ያለ​ውን ያውቅ ነበ​ርና።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዮሐንስ 2:25
9 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

በምትኖርበት በሰማይ ሆነህ ጸሎታቸውን ስማ፤ በደላቸውን ይቅር በል፤ እርዳቸው፤ በሰው ልብና አእምሮ ያለውን ሐሳብ ሁሉ መርምረህ የምታውቅ አንተ ብቻ ነህ፤ ስለዚህ ለእያንዳንዱ ሰው እንደ ሥራው መጠን የሚገባውን ዋጋ ስጠው።


ጌታን በመፍራት ደስ ይለዋል፤ ዐይኑ እንዳየ አይፈርድም፤ ጆሮውም እንደሰማ አይበይንም።


ኢየሱስ ግን ሐሳባቸውን አውቆ እንዲህ አለ “ስለምን በልባችሁ ክፉ ታስባላችሁ?


ወደ ኢየሱስም አመጣው። ኢየሱስም ተመልክቶ “አንተ የዮና ልጅ ስምዖን ነህ፤ አንተ ኬፋ ትባላለህ” አለው፤ ትርጓሜውም “ጴጥሮስ” ማለት ነው።


ኢየሱስ ናትናኤልን ወደ እርሱ ሲመጣ አይቶ ስለ እርሱ “ተንኰል የሌለበት እውነተኛ የእስራኤል ሰው እነሆ!” አለ።


አሳልፎ የሚሰጠውን ያውቅ ነበርና “ሁላችሁ ንጹሐን አይደላችሁም” አለው።


ኢየሱስ ግን ደቀመዛሙርቱ በዚህ ምክንያት እንዳንጐራጐሩ በልቡ አውቆ እንዲህ አላቸው “ይህ ያስናክላችኋልን?


ነገር ግን ከእናንተ የማያምኑ አሉ።” ኢየሱስ የማያምኑት እነማን እንደ ሆኑ፥ አሳልፎ የሚሰጠውም ማን እንደሆነ ከመጀመሪያው ያውቅ ነበርና።


ብዙ ጥፋትና የከፋ ችግር በደረሰባቸው ጊዜ ይህ መዝሙር ምስክር ይሆንባቸዋል። በዘራቸው የሚረሳ አይደለምና። ወደ ማልሁላቸው ምድር ሳላስገ ባቸው በፊት ምን ለማድረግ እንደሚያስቡ እንኳን አስቀድሜ ዐውቃለሁ።”


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች