Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ዮሐንስ 2:2 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

2 ኢየሱስና ደቀ መዛሙርቱም ወደ ሰርጉ ታደሙ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

2 ኢየሱስና ደቀ መዛሙርቱም ወደ ሰርጉ ተጠርተው ነበር።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

2 ኢየሱስና ደቀ መዛሙርቱም ወደ ሠርጉ ተጠርተው ነበር።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

2 ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስና ደቀ መዛ​ሙ​ር​ቱም ወደ ሰርጉ ታደሙ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

2 ኢየሱስም ደግሞ ደቀ መዛሙርቱም ወደ ሰርጉ ታደሙ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዮሐንስ 2:2
30 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

አይከራከርም አይጮህምም፤ ድምፁንም በአደባባይ የሚሰማ የለም።


ንጉሡም እንዲህ ሲል ይመልስላቸዋል ‘እውነት እላችኋለሁ፤ ከሁሉ ለሚያንሱት ከእነዚህ ወንድሞቼ ለአንዱ እንኳ ያደረጋችሁት ለእኔ እንዳደረጋችሁት ነው።’


ያንጊዜ እንዲህ ሲል ይመልስላቸዋል ‘እውነት እላችኋለሁ፤ ከሁሉ ለሚያንሱት ከእነዚህ ለአንዱ ያላደረጋችሁት ለእኔ ደግሞ እንዳላደረጋችሁት ነው።’


ከዚህ በኋላ ከእናቱና ከወንድሞቹ፥ ከደቀ መዛሙርቱም ጋር ወደ ቅፍርናሆም ወረደ፤ በዚያም ለጥቂት ቀን ተቀመጡ።


ደቀ መዛሙርቱም “የቤትህ ቅንዓት ይበላኛል፤” ተብሎ እንደ ተጻፈ አሰቡ።


ስለዚህ ከሙታን ከተነሣ በኋላ ደቀመዛሙርቱ ይህን እንደ ተናገረ አሰቡና መጽሐፍንና ኢየሱስ የተናገረውን ቃል አመኑ።


የወይን ጠጅም ባለቀ ጊዜ የኢየሱስ እናት “የወይን ጠጅ እኮ የላቸውም፤” አለችው።


ከዚህ በኋላ ኢየሱስ ከደቀ መዛሙርቱ ጋር ወደ ይሁዳ አገር መጣ፤ በዚያም ከእነርሱ ጋር ተቀምጦ ያጠምቅ ነበር።


ምንም እንኳን ደቀመዛሙርቱ እንጂ ኢየሱስ እራሱ ባያጠምቅም፤


ስለዚህ ደቀመዛሙርቱ “የሚበላው አንዳች ምግብ ሰው አምጥቶለት ይሆንን?” ተባባሉ።


ደቀመዛሙርቱ ምግብ ሊገዙ ወደ ከተማ ሄደው ነበርና።


ከጠገቡም በኋላ ደቀ መዛሙርቱን “አንድም እንኳን እንዳይጠፋ የተረፈውን ቁርስራሽ አከማቹ፤” አላቸው።


በመሸም ጊዜ ደቀመዛሙርቱ ወደ ባሕር ወረዱ፤


ከደቀ መዛሙርቱም ብዙዎቹ በሰሙ ጊዜ “ይህ ንግግር ከባድ ነው፤ ማን ሊሰማው ይችላል?” አሉ።


በዚህም ምክንያት ከደቀ መዛሙርቱ ብዙዎች ወደ ኋላ ተመለሱ፤ ወደፊትም ከእርሱ ጋር ወደ ፊት መሄድም አቆሙ።


ኢየሱስም ለዐሥራ ሁለቱ “እናንተም መሄድ ትፈልጋላችሁን?” አለ።


ኢየሱስም “እኔ እናንተን ዐሥራ ሁለታችሁን መርጫችሁ የለምን? ከእናንተም አንዱ ዲያብሎስ ነው፤” ብሎ መለሰላቸው።


ስለ ስምዖን ልጅ ስለ አስቆሮቱ ይሁዳ መናገሩ ነበር፤ ከዐሥራ ሁለቱ አንዱ ሲሆን፥ አሳልፎም የሚሰጠው እርሱ ነበርና ነው።


ከደቀ መዛሙርቱ አንዱ የስምዖን ጴጥሮስ ወንድም እንድርያስ እንዲህ አለው፦


ወንድሞቹም “ደቀ መዛሙርትህ ደግሞ የምታደርገውን ሥራ እንዲያዩ ከዚህ ተነሣና ወደ ይሁዳ ሂድ፤


ባገኘውም ጊዜ ወደ አንጾኪያ አመጣው። በቤተ ክርስቲያንም አንድ ዓመት ሙሉ ተሰበሰቡ፤ ብዙ ሕዝብንም አስተማሩ፤ ደቀ መዛሙርትም መጀመሪያ በአንጾኪያ ክርስቲያን ተባሉ።


ደቀ መዛሙርትም እያንዳንዳቸው እንደ ችሎታቸው መጠን አዋጥተው በይሁዳ ለሚኖሩት ወንድሞች እርዳታን ይልኩ ዘንድ ወሰኑ፤


እንግዲህ ስትበሉም ሆነ ስትጠጡ ወይም ማናቸውንም ነገር ስታደርጉ፥ ሁሉን ነገር ለእግዚአብሔር ክብር አድርጉት።


ሚስት ባሏ በሕይወት እስካለ የታሰረች ናት፤ ባሏ ቢሞት ግን በጌታ ይሁን እንጂ የወደደችውን ልታገባ ነጻነት አላት።


በኢየሱስ በኩል እግዚአብሔር አብን እያመሰገናችሁ፥ በቃል ቢሆን ወይም በሥራ የምታደርጉትን ሁሉ በጌታ በኢየሱስ ስም አድርጉት።


ጋብቻ በሁሉ ዘንድ ክቡር፥ መኝታውም ንጹሕ ይሁን፤ ሴሰኞችንና አመንዝሮችን ግን እግዚአብሔር ይፈርድባቸዋል።


እነሆ በደጅ ቆሜ አንኳኳለሁ፤ ማንም ድምፄን ቢሰማ ደጁንም ቢከፍትልኝ፥ ወደ እርሱ እገባለሁ፤ ከእርሱም ጋር እራት እበላለሁ፤ እርሱም ከእኔ ጋር ይበላል።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች