Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ዮሐንስ 19:18 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

18 በዚያም ሰቀሉት፤ ከእርሱም ጋር ሌሎች ሁለት፥ አንዱን በአንድ ጎን፥ አንዱን በሌላ ጎን፥ ኢየሱስንም በመካከላቸው አድርገው ሰቀሉ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

18 በዚያም ሰቀሉት፤ ከርሱም ጋራ ሁለት ሰዎች፣ አንዱን በዚህ በኩል፣ ሌላውን በዚያ በኩል፣ ኢየሱስንም በመካከል አድርገው ሰቀሉ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

18 እዚያ ሰቀሉት፤ ኢየሱስን በመካከል አድርገው፥ ከእርሱ ጋር ሌሎችንም ሁለት ሰዎች በግራና በቀኝ ሰቀሉ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

18 በዚ​ያም ሰቀ​ሉት፤ ከእ​ር​ሱም ጋር አን​ዱን በቀኝ፥ አን​ዱ​ንም በግራ አድ​ር​ገው ሌሎች ሁለት ወን​በ​ዴ​ዎ​ችን ሰቀሉ፤ ኢየ​ሱ​ስ​ንም በመ​ካ​ከ​ላ​ቸው ሰቀሉ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

18 በዚያም ሰቀሉት፥ ከእርሱም ጋር ሌሎች ሁለት፥ አንዱን በዚህ አንዱን በዚያ ኢየሱስንም በመካከላቸው ሰቀሉ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዮሐንስ 19:18
11 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ኃይሌ እንደ ገል ደረቀ፥ በጉሮሮዬም ምላሴ ተጣጋ፥ ወደ ሞትም አፈር አወረድኸኝ።


ስለዚህም እርሱ ብዙዎችን ይወርሳል፥ ከኃያላንም ጋር ምርኮን ይከፋፈላል፤ ነፍሱን ለሞት አሳልፎ ሰጥቶአል፥ ከዓመፀኞችም ጋር ተቈጥሮአል፤ እርሱ ግን የብዙ ሰዎችን ኃጢአት ተሸከመ፥ ስለ ዓመፀኞችም ማለደ።


ከእርሱ ጋር የተሰቀሉት ወንበዴዎችም ደግሞ እንዲህ እያሉ ይሰድቡት ነበር።


ይህም ኢየሱስ በምን ዓይነት ሞት እንደሚሞት ሲያመለክት የተናገረው ቃል ይፈጸም ዘንድ ነብር።


ወታደሮችም መጥተው ከተሰቀሉት ሰዎች መካከል የፊተኛውን ጭን ከእርሱም ጋር የተሰቀለውን የሌላውን ጭን ሰበሩ፤


እርሱንም በእግዚአብሔር በተወሰነው አሳቡና በቀደመው እውቀቱ ተሰጥቶ በዐመፀኞች እጅ ሰቅላችሁ ገደላችሁት።


ክርስቶስ ስለ እኛ እርግማን ሆኖ፥ ከሕግ እርግማን ዋጅቶናል፤ “በእንጨት የሚሰቀል ሁሉ የተረገመ ነው፤” ተብሎ ተጽፎአልና


የእምነታችንንም ራስና ፍጽምና የሆነውን ኢየሱስን እንመልከት፤ እርሱ በፊቱ ስላለው ደስታ መስቀሉን ታግሦ፥ ውርደቱንም ንቆ፥ በእግዚአብሔር ዙፋን ቀኝ ተቀምጦአል።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች