Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ዮሐንስ 17:2 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

2 ይህም በሥጋ ሁሉ ላይ ሥልጣን እንደ ሰጠኸው፥ ለሰጠኸው ሁሉ የዘለዓለምን ሕይወት እንዲሰጣቸው ነው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

2 ከአንተ ለተቀበላቸው ሁሉ የዘላለምን ሕይወት እንዲሰጥ፣ በሰው ሁሉ ላይ ሥልጣን ሰጥተኸዋልና።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

2 የምታከብረውም ለሰጠኸው ሁሉ የዘለዓለም ሕይወትን እንዲሰጥ በሰዎች ሁሉ ላይ ሥልጣን ስለ ሰጠኸው ነው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

2 ሥጋ በለ​በ​ሰው ሁሉ ላይ ሥል​ጣ​ንን እንደ ሰጠ​ኸው መጠን ለሰ​ጠ​ኸው ሁሉ የዘ​ለ​ዓ​ለም ሕይ​ወ​ትን ይሰ​ጣ​ቸው ዘንድ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዮሐንስ 17:2
31 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

የላከኝ የአብ ፈቃድም ይህ ነው፤ ከሰጠኝ ሁሉ አንድም እንኳን እንዳላጠፋ፥ ይልቁንም በመጨረሻው ቀን እንዳስነሣው ነው።


አብ የሚሰጠኝ ሁሉ ወደ እኔ ይመጣል፤ ወደ እኔም የሚመጣውን ከቶ ወደ ውጭ አላስወጣውም፤


አባት ሆይ! ዓለም ሳይፈጠር በፊት ስለ ወደድኸኝ የሰጠኸኝን ክብሬን እንዲያዩ፥ የሰጠኸኝ እነርሱ ደግሞ እኔ ባለሁበት ከእኔ ጋር ይሆኑ ዘንድ እወዳለሁ።


ኢየሱስም ቀረበና እንዲህ አላቸው “ሥልጣን ሁሉ በሰማይና በምድር ተሰጥቶኛል።


የእግዚአብሔር ልጅ እንደመጣ፥ እውነት የሆነውን እንድናውቅ ማስተዋልን እንደ ሰጠን እናውቃለን፤ እውነት በሆነው በእርሱ እንኖራለን፥ እርሱም ልጁ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው። እርሱ እውነተኛ አምላክና የዘለዓለም ሕይወት ነው።


እኔ ስለ እነርሱ እለምናለሁ፤ ስለ ሰጠኸኝ ስለ እነርሱ እንጂ ስለ ዓለም አልለምንም፤ እነርሱ የአንተ ናቸውና፤


“ከዓለም ወስጥ ለሰጠኸኝ ሰዎች ስምህን ገለጥሁላቸው። የአንተ ነበሩ፤ ለእኔም ሰጠሃቸው፤


እኔ ከምሰጠው ውሃ የሚጠጣ ሁሉ ግን ለዘለዓለም አይጠማም፤ እኔ የምሰጠው ውሃ በእርሱ ውስጥ ለዘለዓለም ሕይወት የሚፈልቅ የውሃ ምንጭ ይሆናል እንጂ፤” አላት።


አባት ልጁን ይወዳል፥ ሁሉንም በእጁ ሰጥቶታል።


እርሱ የሰጠን ተስፋ ይህ ነው፥ እርሱም የዘለዓለም ሕይወት ነው።


እርሱም ወደ ሰማይ ሄዶ በእግዚአብሔር ቀኝ አለ፤ መላእክትና ሥልጣናት ኀይላትም ተገዝተውለታል።


በእነዚህ በኋለኞቹ ዘመናት ግን፥ ሁሉን ወራሽ ባደረገው ደግሞም ዓለማትን በፈጠረበት በልጁ ለእኛ ተናገረን፥፥


ሁሉም ነገር በአባቴ ለእኔ ተሰጥቶአል፤ ከአብ በቀር ወልድን የሚያውቅ የለም፤ ከወልድና ወልድም ሊገለጥለት ከሚፈቅደው በቀር አብን የሚያውቅ የለም።


ወደ ዘለዓለም ሕይወት የሚያደርሰውን የጌታችንን የኢየሱስ ክርስቶስን ምሕረት ስትጠባበቁ ሳለ፥ በእግዚአብሔር ፍቅር ራሳችሁን ጠብቁ።


ሕይወትም ተገለጠ፥ አይተነዋል እንመሰክራለንም፥ በአብ ዘንድ የነበረውን ለእኛም የተገለጠውን የዘለዓለምን ሕይወት እናወራላችኋለን፤


ነገር ግን ክርስቶስ ኢየሱስ ዋነኛ በምሆን በእኔ ላይ ትዕግስቱን ሁሉ በማሳየት፥ በእርሱ አምነው የዘለዓለም ሕይወትን ለሚያገኙ ምሳሌ እንድሆን አደረገኝ፥ በእዚህም ምክንያት ምሕረትን አገኘሁ።


በዚህም በሰማይና በምድር ከምድርም በታች ያሉት ሁሉ በኢየሱስ ስም እንዲንበረከኩና


ይህን ኃይል እርሱ ክርስቶስን ከሙታን ሲያስነሣውና በሰማያዊ ስፍራ በቀኙ ሲያስቀምጠው የታየ ነው።


ጠላቶቹን ሁሉ ከእግሩ ሥር እስከሚያደርግ ድረስ ሊነግሥ ይገባዋልና።


የኃጢአት ደመወዝ ሞት ነውና፥ የእግዚአብሔር የጸጋ ስጦታ ግን በጌታችን በክርስቶስ ኢየሱስ የዘለዓለም ሕይወት ነው።


የዳዊት መዝሙር። ጌታ ጌታዬን፦ “ጠላቶችህን ለእግርህ መቀመጫ እስካደርግልህ ድረስ በቀኜ ተቀመጥ አለው።”


ለሚጠፋ መብል አትሥሩ፤ ነገር ግን የለዘለዓለም ሕይወት ለሚሆነው መብል ሥሩ፤ ይህም የሰው ልጅ ለሚሰጣችሁ ነው፤ እርሱን እግዚአብሔር አብ አትሞታልና።”


እነዚህ ወደ ዘለዓለም ቅጣት፥ ጻድቃን ግን ወደ ዘለዓለም ሕይወት ይሄዳሉ።”


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች