ዮሐንስ 16:7 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)7 እኔ ግን እውነት እነግራችኋለሁ፤ እኔ ብሄድ ይሻላችኋል። እኔ ባልሄድ አጽናኙ ወደ እናንተ አይመጣምና፤ እኔ ብሄድ ግን እርሱን እልክላችኋለሁ። ምዕራፉን ተመልከትአዲሱ መደበኛ ትርጒም7 ነገር ግን፣ እውነት እላችኋለሁ፤ መሄዴ ይበጃችኋል። እኔ ካልሄድሁ አጽናኙ ወደ እናንተ አይመጣም፤ ከሄድሁ ግን እርሱን ወደ እናንተ እልካለሁ፤ ምዕራፉን ተመልከትአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም7 እኔ ግን እውነት፥ እውነት እላችኋለሁ፤ የእኔ መሄድ ለእናንተ ይጠቅማችኋል፤ እኔ ካልሄድኩ አጽናኙ ወደ እናንተ አይመጣም፤ እኔ ከሄድኩ ግን እርሱን እልክላችኋለሁ። ምዕራፉን ተመልከትየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)7 “እኔ በእውነት የሚሆነውን እነግራችኋለሁ፤ እኔ ብሄድ ይሻላችኋል፤ እኔ ካልሄድሁ ጰራቅሊጦስ ወደ እናንተ አይመጣምና፤ እኔ ከሄድሁ ግን እርሱን እልክላችኋለሁ። ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)7 እኔ ግን እውነት እነግራችኋለሁ፤ እኔ እንድሄድ ይሻላችኋል። እኔ ባልሄድ አጽናኙ ወደ እናንተ አይመጣምና፤ እኔ ብሄድ ግን እርሱን እልክላችኋለሁ። ምዕራፉን ተመልከት |