Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ዮሐንስ 14:21 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

21 ትእዛዜ በእርሱ ዘንድ ያለችው የሚጠብቃትንም የሚወደኝ እርሱ ነው፤ የሚወደኝንም አባቴ ይወደዋል፤ እኔም እወደዋለሁ ራሴንም እገልጥለታለሁ።”

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

21 የሚወድደኝ ትእዛዜን ተቀብሎ የሚጠብቅ ነው፤ የሚወድደኝንም አባቴ ይወድደዋል፤ እኔም እወድደዋለሁ፤ ራሴንም እገልጥለታለሁ።”

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

21 “እኔን የሚወደኝ ትእዛዜን የሚቀበልና በሥራ ላይ የሚያውለው ነው፤ እኔንም የሚወደኝን አባቴ ይወደዋል፤ እኔም እወደዋለሁ፤ ራሴንም እገልጥለታለሁ።”

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

21 ትእ​ዛዜ በእ​ርሱ ዘንድ ያለ የሚ​ጠ​ብ​ቀ​ውም የሚ​ወ​ደኝ እርሱ ነው፤ የሚ​ወ​ደ​ኝ​ንም አባቴ ይወ​ደ​ዋል፤ እኔም እወ​ደ​ዋ​ለሁ፤ ራሴ​ንም እገ​ል​ጥ​ለ​ታ​ለሁ።”

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

21 ትእዛዜ በእርሱ ዘንድ ያለችው የሚጠብቃትንም የሚወደኝ እርሱ ነው፤ የሚወደኝንም አባቴ ይወደዋል እኔም እወደዋለሁ ራሴንም እገልጥለታለሁ።”

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዮሐንስ 14:21
43 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

“የምትወዱኝ ከሆነ ትእዛዜን ትጠብቃላችሁ።


ትእዛዛቱን እንድንጠብቅ፥ የእግዚአብሔር ፍቅር ይህ ነውና፤ ትእዛዛቱም ከባዶች አይደሉም።


ቃሉን የሚጠብቅ ግን በእውነት የእግዚአብሔርን ፍቅር በእርሱ ፍጹም ሆኗል። በእርሱ እንዳለን በዚህ እናውቃለን።


ፍቅር ይህ ነው፥ እርሱም በትእዛዛቱ መመላለስ ነው፤ ትእዛዙ ይህ ነው፥ ከመጀመሪያ ጀምሮ እንደ ሰማችሁት፥ በእርሱ ተመላለሱ።


“ጌታ አምላክህን በመውደድ ዛሬ እኔ የምሰጣችሁን ትእዛዞች በታማኝነት ብትጠብቁ፥ በፍጹም ልባችሁ፥ በፍጹም ነፍሳችሁም እርሱን በማገልገል፥ በታማኝነት ብትጠብቁ፥


ምክንያቱም አብ እራሱ ስለሚወዳችሁ ነው፤ ይህም እናንተ ስለ ወደዳችሁኝና ከእግዚአብሔርም ዘንድ እኔ እንደመጣሁ ስላመናችሁ ነው።


እርሱ ግን፦ “በእርግጥ ብፁዓንስ የእግዚአብሔርን ቃል ሰምተው የሚጠብቁት ናቸው፤” አለ።


እኔ ያዘዝኋችሁን ሁሉ ብታደርጉ እናንተ ወዳጆቼ ናችሁ።


እነሆ በደጅ ቆሜ አንኳኳለሁ፤ ማንም ድምፄን ቢሰማ ደጁንም ቢከፍትልኝ፥ ወደ እርሱ እገባለሁ፤ ከእርሱም ጋር እራት እበላለሁ፤ እርሱም ከእኔ ጋር ይበላል።


ወደ ሕይወት ዛፍ ለመድረስ ሥልጣን እንዲኖራቸው፥ በደጆችዋም ወደ ከተማይቱም እንዲገቡ ልብሳቸውን የሚያጥቡ ብፁዓን ናቸው።


በክርስቶስ ፊት የእግዚአብሔርን የክብሩን እውቀት እንዲሰጥ ብርሃን በልባችን ውስጥ ያበራ፥ “በጨለማ ብርሃን ይብራ፤” ያለው እግዚአብሔር ነው።


መንፈስ ለአብያተ ክርስቲያናት የሚናገረውን ጆሮ ያለው ይስማ። ድል ለነሣው ከተሰወረ መና እሰጠዋለሁ፤ ነጭ ድንጋይንም እሰጠዋለሁ፤ በድንጋዩም ላይ ከተቀበለው በቀር ማንም የማያውቀው አዲስ ስም ተጽፎአል።


ይህም እኔ በእነርሱ አንተም በእኔ ስትሆን፥ በፍጹም አንድ እንዲሆኑ፥ እንዲሁም አንተ እንደ ላክኸኝና በወደድኸኝም መጠን እነርሱን እንደ ወደድሃቸው ዓለም እንዲያውቅ ነው።


ጽድቄን የሚወድዱአት ደስ ይበላቸው ሐሴትንም ያድርጉ፥ የባርያውን ሰላም የሚወድድ ጌታ ታላቅ ይሁን ዘወትር ይበሉ።


የእግዚአብሔር ልጆች ተብለን እንድንጠራ አብ እንዴት ያለውን ፍቅር እንደ ሰጠን እዩ፤ እንዲሁም ነን። ዓለም እርሱን ስላላወቀው እኛንም አያውቀንም።


ጌታ አምላክሽ በመካከልሽ ኃያል ታዳጊ ነው፤ በአንቺም በፍጹም በደስታ ደስ ይለዋል፥ በፍቅሩም ያርፋል፥ በእልልታም በአንቺ ደስ ይለዋል።”


ራሱ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስና፥ የወደደን በጸጋም የዘለዓለምን መጽናናትና መልካሙን ተስፋ የሰጠን እግዚአብሔር አባታችን


“እነሆ፥ ከእስራኤል ቤትና ከይሁዳ ቤት ጋር አዲስ ቃል ኪዳን የማደርግበት ወራት ይመጣል፥ ይላል ጌታ፤


እርሱ ያከብረኛል፤ የእኔ ከሆነው ወስዶ ይነግራችኋልና።


“ወላጆች እንደሌላቸው ልጆች አልተዋችሁም፤ ወደ እናንተ እመጣለሁ።


ጌታ ከመንፈስህ ጋር ይሁን። ጸጋ ከእናንተ ጋር ይሁን፤ አሜን።


እኛም ሁላችን፥ በመጋረጃ በማይሸፈን ፊት፥ የጌታን ክብር እንደ መስተዋት እያብለጨለጭን፥ የእርሱን መልክ እንድንመስል ከክብር ወደ ክብር እንለወጣለን፥ ይህም መንፈስ ከሚሆን ጌታ የመጣ ነው።


እርሱም ‘ፍጠን፤ ከኢየሩሳሌምም ቶሎ ውጣ፤ ስለ እኔ የምትመሰክረውን አይቀበሉህምና፤’ ሲለኝ አየሁት።


ይህ ነገር ከእኔ እንዲለይ ሦስት ጊዜ ጌታን ለመንሁ።


እርሱም፦ “እባክህ ክብርህን አሳየኝ” አለ።


ይወድድህማል፥ ይባርክህማል፥ ያበዛህማል፤ ይሰጥህም ዘንድ ለአባቶችህ በማለላቸው ምድር የሆድህን ፍሬ እንዲሁም የምድርህንም ፍሬ፥ እህልና ወይንህን፥ ዘይትህንም፥ በከብትም ብዛት በበግም መንጋ አብዝቶ ይባርክልሃል።


እኔ የሚወድዱኝን እወድዳለሁ፥ ተግተው የሚሹኝም ያገኙኛል።


ሕዝቅያስ ለእግዚአብሔር ታማኝ ስለ ሆነ ከእርሱ መንገድ የራቀበት ጊዜ የለም፤ እግዚአብሔር ለሙሴ የሰጣቸውን ትእዛዞች ሁሉ በጥንቃቄ ይፈጽም ነበር።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች