Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ዮሐንስ 12:15 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

15 “አንቺ የጽዮን ልጅ አትፍሪ፤ እነሆ፥ ንጉሥሽ በአህያ ውርንጫ ላይ ተቀምጦ ይመጣል፤” ተብሎ እንደ የተጻፈው እንዲፈጸም ነው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

15 “የጽዮን ልጅ ሆይ፤ አትፍሪ፤ እነሆ፤ ንጉሥሽ በአህያ ግልገል ተቀምጦ ይመጣል።”

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

15 “አንቺ የጽዮን ከተማ፥ ኢየሩሳሌም ሆይ አትፍሪ! እነሆ! ንጉሥሽ በአህያ ውርንጭላ ላይ ተቀምጦ ይመጣል” ተብሎ የተጻፈው ትንቢት እንዲፈጸም ነው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

15 “የጽ​ዮን ልጅ ሆይ፥ አት​ፍሪ፤ እነሆ፥ ንጉ​ሥሽ በአ​ህያ ውር​ንጫ ተቀ​ምጦ ይመ​ጣል” ተብሎ እንደ ተጻፈ፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዮሐንስ 12:15
17 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

አንቺ የጽዮን ልጅ ሆይ፥ እጅግ ደስ ይበልሽ! አንቺ የኢየሩሳሌም ልጅ ሆይ፥ እልል በዪ! እነሆ፥ ንጉሥሽ ጻድቅና አዳኝ ነው፤ ትሑትም ሆኖ በአህያም፥ በአህያይቱ ግልገል በውርጫይቱ ላይ ተቀምጦ ወደ አንቺ ይመጣል።


እነሆ፥ ጌታ ለምድር ዳርቻ አዋጅ እንዲህ ብሎ ነግሮአል፦ ለጽዮን ልጅ፦ “እነሆ፥ መድኃኒትሽ ይመጣል፤ እነሆ፥ ዋጋው ከእርሱ ጋር፥ ሥራውም በፊቱ አለ” በሏት።


ንጉሡም ጺባን፥ “ይህን ያመጣኸው ለምንድን ነው?” ሲል ጠየቀው። ጺባም “አህዮቹን የንጉሡ ቤተሰቦች እንዲቀመጡባቸው፥ ዳቦውንና ፍራፍሬውን ወጣቶቹ እንዲበሉት፥ የወይን ጠጁን ደግሞ በምድረ በዳ የደከሙት እንዲጠጡት ነው” አለው።


አንተ የመንጋው ግንብ ሆይ፥ የጽዮን ሴት ልጅ ምሽግ ሆይ፥ የቀደመችው ግዛት፥ የኢየሩሳሌም ሴት ልጅ መንግሥት ወደ አንተ ትገባለች።


አንተ ትል ያዕቆብ፥ ታናሽ እስራኤል ሆይ፥ አትፍራ፤ እረዳሃለሁ፥ ይላል ጌታ፥ የሚቤዥህም የእስራኤል ቅዱስ ነው።


ንጉሡም አላቸው፦ “የጌታችሁን ባርያዎች ይዛችሁ ሂዱ፥ ልጄንም ሰሎሞንን በበቅሎዬ ላይ አስቀምጡት፥ ወደ ግዮንም አውርዱት፥


እርሱም በሰባ አህዮች ላይ የሚቀመጡ አርባ ወንዶች ልጆችና ሠላሳ ወንዶች የልጅ ልጆች ነበሩት፤ በእስራኤልም ላይ ስምንት ዓመት ፈራጅ ሆነ።


በነጫጭ አህዮች ላይ የምትጫኑ፥ በወላንሳ ላይ የምትቀመጡ፥ በመንገድም የምትሄዱ፥ ተናገሩ።


ንጉሡም ብዙ ፈረሶችን ለራሱ አያብዛ፤ ወይም ደግሞ ፈረሰኞች ለማብዛት ሕዝቡን ወደ ግብጽ አይመልስ፤ ጌታ፥ ‘በዚያ መንገድ ፈጽሞ አትመለሱ’ ብሎአችኋልና።


ከዚህ በኋላ አቤሴሎም ሠረገላና ፈረሶች፥ ፊት ፊቱም የሚሮጡ አምሳ ሰዎች አዘጋጀ።


“ለጽዮን ልጅ “እነሆ፥ ንጉሥሽ የዋህ ሆኖ በአህያ ላይና በአህያይቱ ግልገል በውርንጫ ላይ ተቀምጦ ወደ አንቺ ይመጣል፥ በሉአት።”


ኢየሱስ የአህያ ውርንጭላ አግኝቶ በእርሱ ላይ ተቀመጠ፤ ይህም፥


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች