Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ኢዩኤል 3:12 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

12 አሕዛብ ይነሡ፥ ወደ ኢዮሣፍጥ ሸለቆም ይውጡ፥ በዙሪያ ባሉ አሕዛብ ሁሉ ላይ እፈርድ ዘንድ በዚያ እቀመጣለሁና።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

12 “ሕዝቦች ይነሡ፤ ወደ ኢዮሣፍጥም ሸለቆ ፈጥነው ይውረዱ፤ ዙሪያውን ባሉት ሕዝቦች ሁሉ ላይ ልፈርድ፣ በዚያ እቀመጣለሁና።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

12 “አሕዛብ ሁሉ ተነሣሥተው ወደ ኢዮሣፍጥ ሸለቆ ይሂዱ፤ እኔ እግዚአብሔር በዙሪያ ባሉት አሕዛብ ላይ ለመፍረድ እዚያ እቀመጣለሁ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

12 “አሕ​ዛብ ሁሉ ይነሡ፤ ወደ ኢዮ​ሣ​ፍጥ ሸለ​ቆም ይውጡ፤ በዙ​ሪያ ባሉ አሕ​ዛብ ሁሉ ላይ እፈ​ርድ ዘንድ በዚያ እቀ​መ​ጣ​ለ​ሁና።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

12 አሕዛብ ይነሡ፥ ወደ ኢዮሣፍጥ ሸለቆም ይውጡ፥ በዙሪያ ባሉ አሕዛብ ሁሉ ላይ እፈርድ ዘንድ በዚያ እቀመጣለሁና።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ኢዩኤል 3:12
17 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

አሕዛብን ሁሉ ሰብስቤ ወደ ኢዮሣፍጥ ሸለቆ አወርዳቸዋለሁ፥ በዚያም ስለ ሕዝቤና ስለ ርስቴ ስለ እስራኤል በአሕዛብ መካከል የበተኑአቸውን፥ ምድሬንም የተካፈሉአትን እፈርድባቸዋለሁ።


ጌታ በፍርድ ወንበር ላይ ተቀምጦአል፤ በሕዝቡም ላይ ለመፍረድ ተነሥቶአል።


እርሱ በሕዝቦች መካከል ይፈርዳል፤ የብዙ ሰዎችን አለመግባባት ያስወግዳል። እነርሱም ሰይፋቸውን ቀጥቅጠው ማረሻ ጦራቸውንም ማጭድ ያደርጋሉ። ሕዝብ በሕዝብ ላይ ሰይፍ አያነሣም፤ ጦርነትንም ከእንግዲህ አይማሩም።


ዓለምንም በጽድቅ አሕዛብንም በቅንነት ይፈርዳል።


ይመጣልና፥ በምድር ላይ ሊፈርድ ይመጣልና፥ እርሱም ዓለምን በጽድቅ አሕዛብንም በቅንነት ይፈርዳል።


በዚያም ቀን የእግዚአብሔር እግሮች በኢየሩሳሌም ትይዩ በምሥራቅ በኩል ባለው በደብረ ዘይት ተራራ ላይ ይቆማሉ፤ የደብረ ዘይት ተራራም በመካከሉ ወደ ምሥራቅና ወደ ምዕራብ ይሰነጠቃል፥ እጅግም ጥልቅ ሸለቆ ይሆናል፤ የተራራውም እኩሌታ ወደ ሰሜን፥ እኩሌታውም ወደ ደቡብ ይሸሻል።


በብዙዎች ሕዝቦች መካከል ይፈርዳል፥ በሩቅም ባሉ በብርቱዎች መንግሥታት ላይ ይበይናል፤ ሰይፋቸውን ወደ ማረሻ፥ ጦራቸውን ወደ ማጭድ ለመለወጥ ይቀጠቅጣሉ፤ መንግሥት በመንግሥት ላይ ሰይፍ አያነሣም፥ ከእንግዲህ ወዲህ ጦርነት አይማሩም።


የጌታ ቀን በፍርድ ሸለቆ ቀርቧልና የብዙ ብዙ ሕዝብ ውካታ በፍርድ ሸለቆ አለ።


ጠላት ነፍሴን ያሳድዳት ያግኛትም፥ ሕይወቴንም በምድር ላይ ይርገጣት፥ ክብሬንም በትቢያ ላይ ያዋርዳት።


ሰማይም ተከፍቶ አየሁ፤ እነሆም ነጭ ፈረስ፤ የተቀመጠበትም የታመነና እውነተኛ ይባላል፤ በጽድቅም ይፈርዳል፤ ይዋጋልም።


በዚያም ቀን በእስራኤል፥ በባሕሩ በምሥራቅ በኩል ባለው በመንገደኞች ሸለቆ ለጎግ የመቃብር ስፍራ እሰጠዋለሁ፤ በዚያም ጎግንና ብዛቱን ሁሉ ስለሚቀበሩ፥ የመንገደኞች መተላለፊያ ይዘጋል፤ “የሐሞን-ጎግ ሸለቆ” ተብሎ ይጠራል።


ቀኑ ቅርብ ነውና፥ የጌታ ቀን ቅርብ ነው፥ የደመና ቀን፥ የሕዝቦች ጊዜ ይሆናል።


በአራተኛውም ቀን በበረከት ሸለቆ ውስጥ ተሰበሰቡ፥ በዚያም ጌታን ባረኩ፤ ስለዚህም ያ ስፍራ እስከ ዛሬ ድረስ የበረከት ሸለቆ ተባለ።


ስለ ራእይ ሸለቆ የተነገረ ራእይ። እናንተ ሁላችሁ ወደ ሰገነት መውጣታችሁ ምን ማለት ነው?


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች