Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ኢዩኤል 2:7 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

7 እንደ ኃያላን ይሮጣሉ፥ እንደ ጦር ሰዎችም በቅጥሩ ላይ ይወጣሉ፥ እያንዳንዱም በመንገዱ ላይ ይራመዳል፥ ከእርምጃቸውም አያፈገፍጉም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

7 እንደ ተዋጊዎች ድንገት አደጋ ይጥላሉ፤ እንደ ወታደሮችም ቅጥርን ይዘልላሉ፤ ከመንገዳቸውም ሳይወጡ፣ አቅጣጫ ይዘው ይጓዛሉ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

7 እንደ ጦረኞች ይጋፈጣሉ፤ እንደ ተዋጊዎችም ቅጽርን ይዘላሉ፤ ሁሉም ቀጥ ብለው ወደ ፊት ይጓዛሉ፤ በማመንታት አቅጣጫቸውን አይለውጡም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

7 እንደ ተዋ​ጊ​ዎች ይሮ​ጣሉ፤ እንደ ጦረ​ኞ​ችም በቅ​ጥሩ ላይ ይወ​ጣሉ፤ እያ​ን​ዳ​ን​ዱም በመ​ን​ገዱ ላይ ይራ​መ​ዳል፤ ከእ​ር​ም​ጃ​ቸ​ውም አያ​ፈ​ገ​ፍ​ጉም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

7 እንደ ኃያላን ይሮጣሉ፥ እንደ ሰልፈኞችም በቅጥሩ ላይ ይወጣሉ፥ እያንዳንዱም በመንገዱ ላይ ይራመዳል፥ ከእርምጃቸውም አያፈገፍጉም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ኢዩኤል 2:7
11 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

አንበጣዎች ንጉሥ የላቸውም፥ ሁላቸውም ግን በመልካም ሥርዓት ይሄዳሉ።


በከተማም ያኰበኩባሉ፥ በቅጥሩም ላይ ይሮጣሉ፥ ወደ ቤቶችም ይወጣሉ፥ እንደ ሌባም በመስኮቶች ይገባሉ።


“በወይኗ ትልሞች በመካከል ሂዱና አበላሹ፥ ነገር ግን ፈጽማችሁ አታጥፉ፤ የጌታ አይደሉምና ቅርንጫፍዋን ውሰዱ።


በዚያም ዕለት ዳዊት፥ “ኢያቡሳውያንን መግደል የሚፈልግ፥ የዳዊት ጠላቶች ወደሚሆኑ፥ ‘አንካሶችና ዕውሮች’ ለመድረስ በውሃ መተላለፊያው ይውጣ” አለ። ለዚህም ነበር፥ “አንካሶችና ዕውሮች ወደ ቤተ መንግሥት አይገቡም” የተባለው።


ሳኦልና ዮናታን፥ የተዋደዱና የተስማሙ፤ በሕይወትም ሆነ በሞት ያልተለያዩ፤ ከንስርም ይልቅ የፈጠኑ፥ ከአንበሳም ይልቅ ብርቱዎች ነበሩ።


ድምፃቸው ወደ ምድር ሁሉ፥ ቃላቸውም እስከ ዓለም ዳርቻ ወጣ። በእነርሱም ውስጥ የፀሐይን ድንኳን አደረገ፥


በቁስል ላይ ቁስል ጨመረብኝ፥ እንደ ኃያል እየሠገገ ይሮጥብኛል።


አንዱ ካንዱ ጋር አይጋፋም፥ እያንዳንዱም መንገዱን ይጠበጥባል፥ በጦር መሣርያ መካከል ያልፋሉ፥ የሚያስቆማቸው ነገር የለም።


በጽኑ የሠለጠኑ ተዋጊዎች፥ ለውጊያም የተዘጋጁ የአሴር ሰዎች አርባ ሺህ ነበሩ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች