Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ኢዮብ 38:12 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

12 በውኑ ከተወለድህ ጀምሮ ማለዳን አዝዘህ ታውቃለህን? ለወገግታም ስፍራውን አስታውቀኸዋልን?

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

12 “ከተወለድህ ጀምሮ ንጋትን አዝዘህ ታውቃለህን? ወይስ ወጋገን ስፍራውን እንዲይዝ አድርገሃል?

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

12 ኢዮብ ሆይ! በሕይወት ዘመንህ ሁሉ ከቶ ንጋትን አዘህ ታውቃለህን? ለንጋት ወገግታስ ቦታ መድበህለታልን?

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

12 “የን​ጋት ወገ​ግታ በአ​ንተ ተፈ​ጥ​ሮ​አ​ልን? የአ​ጥ​ቢያ ኮከ​ብስ ትእ​ዛ​ዙን በአ​ንተ ዐው​ቋ​ልን?

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

12-13 የምድርን ዳርቻ ይይዝ ዘንድ፥ ከእርስዋም በደለኞች ይናወጡ ዘንድ፥ በውኑ ከተወለድህ ጀምሮ ማለዳን አዝዘሃልን? ለወገግታም ስፍራውን አስታውቀኸዋልን?

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ኢዮብ 38:12
14 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ቀኑ የአንተ ነው ሌሊቱም የአንተ ነው፥ አንተ ፀሓዩንና ጨረቃውን አዘጋጀህ።


እኛ የትናንት ብቻ ነን፥ ምንም አናውቅም፤ ቀኖቻችን በምድር ላይ እንደ ጥላ ናቸውና።


እግዚአብሔርም ብርሃኑን ቀን ብሎ ጠራው፥ ጨለማውንም ሌሊት አለው። ማታም ሆነ ጥዋትም ሆነ፥ አንደኛ ቀን።


ደግሞም ይህን የበለጠ የሚያረጋግጥ የነቢያት ቃል አለ፤ ጎሕ እስኪቀድ ድረስ የንጋትም ኮከብ በልባችሁ እስኪገለጥ፥ ሰው በጨለማ ስፍራ የሚበራን መብራት እንደሚያስተውል ቃሉን ልብ በማለት መልካም ታደርጋላችሁ።


በአምላካችን የርኅራኄ ምሕረት ከላይ የሚመጣው ብርሃን ይጐበኘናልና፤


በዚያን ጊዜ ተወልደህ ነበርና፥ የዕድሜህም ቍጥር ብዙ ነውና፥ በእውነት አንተ ሳታውቅ አትቀርም።


ምድርን በመሠረትሁ ጊዜ አንተ የት ነበርህ? ታስተውል እንደሆንህ ተናገር።


“በውኑ መጀመሪያ የተወለደው የሰው ልጅ አንተ ነህን? ከተራሮች በፊትስ ተፀንሰሀልን?


እስከዚህ ድረስ ድረሺ፥ አትለፊ፥ በዚህም ለትዕቢተኛው ማዕበልሽ ገደብ ይሁን አልሁ።


የምድርን ዳርቻ ይይዝ ዘንድ፥ ከእርሷም በደለኞች ይናወጡ ዘንድ፥


ሰባቱን ከዋክብትና ኦሪዮን የተባለውን ኮበብ የፈጠረ፥ የሞትን ጥላ ወደ ንጋት የሚለውጥ፥ ቀኑንም በሌሊት የሚያጨልም፥ የባሕሩንም ውኆች ጠርቶ በምድር ፊት ላይ የሚያፈስሳቸው እርሱ፥ ስሙ ጌታ ነው።


ቤቶቹን በጨለማ ይሰረስራሉ፥ በቀን ይሸሸጋሉ፥ ብርሃንም አያውቁም።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች