Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ኢዮብ 29:9 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

9 መኮንኖች ከመናገር ዝም ይሉ፥ እጃቸውንም በአፋቸው ላይ ይጭኑ ነበር።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

9 የሰፈሩ ታላላቅ ሰዎች ከመናገር ይቈጠቡ፣ እጃቸውንም በአፋቸው ላይ ይጭኑ ነበር፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

9 ሲነጋገሩ የነበሩ የሕዝብ መሪዎችም እኔን ሲያዩ እጆቻቸውን በአፋቸው ላይ አድርገው ጸጥ ይሉ ነበር።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

9 ኀያ​ላ​ኑም ከመ​ና​ገር ዝም አሉ፥ እጃ​ቸ​ው​ንም በአ​ፋ​ቸው ላይ ጫኑ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

9 አለቆቹ ከመናገር ዝም አሉ፥ እጃቸውንም በአፋቸው ላይ ጫኑ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ኢዮብ 29:9
10 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ወደ እኔ ተመልከቱ፥ ተደነቁም፥ እጃችሁንም በአፋችሁ ላይ አኑሩ።


ሰዎች እኔን ሰምተው በትዕግሥት ተጠባበቁ፥ ምክሬንም ለማዳመጥ ዝም አሉ።


ወጣቶች እኔን አይተው ይሸሸጉ፥ ሽማግሌዎችም ተነሥተው ይቆሙ ነበር።


“አንድ ሰው ከአንተ ጋር ለመናገር ቢሞክር ትቀየማለህን? ቃልንስ ከመናገር ማን ሊቀር ይችላል?


“እነሆ፥ እኔ ወራዳ ሰው ነኝ፥ የምመልስልህ ምንድነው? እጄን በአፌ ላይ እጭናለሁ።


“ስለዚህም ከመናገር አፌን አልከለክልም፥ በመንፈሴ ጭንቀትን እናገራለሁ፥ በነፍሴ ምሬት በኀዘን አንጐራጉራለሁ።


በቃል ብዛት ውስጥ መተላለፍ ሳይኖር አይቀርም፥ ከንፈሩን የሚገታ ግን አስተዋይ ነው።


ከፍ ከፍ በማለት የተሞኝህ እንደሆነ፥ ክፉም ያሰብህ እንደሆነ፥ እጅህን በአፍህ ላይ ጫን።


የተወደዳችሁ ወንድሞቼ ሆይ! ይህን አትርሱ፥ ሰው ሁሉ ለመስማት የፈጠነ፥ ለመናገርም የዘገየ፥ ለቁጣም የዘገየ ይሁን፤


እነርሱም፥ “ዝም በል አንዲት ቃል እንዳትተነፍስ፤ ከእኛ ጋር ሁን፤ አባትም ካህንም ሁነን፤ ለአንተስ የአንድ ቤተሰብ ካህን ከመሆን ይልቅ በእስራኤል የአንዱ ነገድና ጐሣ ካህን ሆነህ ማገልገሉ አይሻልህምን?” አሉት።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች