ኢዮብ 22:3 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)3 ጻድቅ መሆንህስ ሁሉን የሚችለውን አምላክ ደስ ያሰኘዋልን? መንገድህን ማቅናትህስ ይጠቅመዋልን? ምዕራፉን ተመልከትአዲሱ መደበኛ ትርጒም3 አንተ ጻድቅ ብትሆን ሁሉን ቻዩን አምላክ ምን ደስ ታሠኘዋለህ? መንገድህ ያለ ነቀፋ ቢሆንስ የሚተርፈው ምንድን ነው? ምዕራፉን ተመልከትአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም3 የአንተ መልካም ሥራ ሁሉን ለሚችል አምላክ ምን ይጠቅመዋል? የኑሮህስ ፍጹምነት ለእርሱ ምን ይረባዋል? ምዕራፉን ተመልከትየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)3 አንተ በሥራህ ንጹሕ ከሆንህ እግዚአብሔርን ምን ያገደዋል? መንገድህንስ ብታቀና ምን ይጠቅመዋል? ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)3 ጻድቅ መሆንህስ ሁሉን የሚችለውን አምላክ ደስ ያሰኘዋልን? መንገድህን ማቅናትህስ ይጠቅመዋልን? ምዕራፉን ተመልከት |
ጠቢብ ብትሆን ለራስህ ጠቢብ ትሆናለህ፥ ፌዘኛም ብትሆን ፌዘኛነትህን ለብቻህ ትሸከማለህ። (የሚቀጥለው ከግሪክ የተጨመረ ነው።) ልጄ ለራስህ አዋቂ ብትሆን ለባልንጀራህም አዋቂ ትሆናለህ፥ ለራስህ ክፉ ብትሆን ግን ክፋትን ለብቻህ ትሸከማለህ። ሐሰትን የሚያዘጋጅ ሰው ነፋሳትን እንደሚገዛ ነው፥ የሚበርር ወፍንም እንደሚከተል ይመስላል። የወይኑ ቦታ መንገዱን ረስቷልና፥ የሚሠማራባትን መንገድ እንዲስት አድርጓልና፥ ወደ ምድረ በዳ ይሄዳል፥ ለጥም ወደ ተሠራች አገር ይሄዳል፥ የማያፈራ የማይጠቅም ገንዘብንም በእጁ ይሰበስባል።