ኢዮብ 22:2 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)2 “በውኑ ሰው እግዚአብሔርን ይጠቅመዋልን? ይልቁንም ጥበበኛ ሰው ራሱን ይጠቅማል። ምዕራፉን ተመልከትአዲሱ መደበኛ ትርጒም2 “ሰው እግዚአብሔርን ሊጠቅም ይችላልን? ጠቢብ እንኳ ቢሆን ምን ይጠቅመዋል? ምዕራፉን ተመልከትአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም2 “ሰው እግዚአብሔርን ሊጠቅም ይችላልን? ሌላው ቀርቶ ጠቢብ እንኳ ቢሆን ጥቅሙ ለራሱ እንጂ ለእግዚአብሔር አይሆንም። ምዕራፉን ተመልከትየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)2 “በውኑ ማስተዋልንና ዕውቀትን የሚያስተምር፥ እግዚአብሔር አይደለምን? ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)2 በውኑ ሰው እግዚአብሔርን ይጠቅመዋልን? በእውነት ጥበበኛ ሰው ራሱን ይጠቅማል። ምዕራፉን ተመልከት |
ጠቢብ ብትሆን ለራስህ ጠቢብ ትሆናለህ፥ ፌዘኛም ብትሆን ፌዘኛነትህን ለብቻህ ትሸከማለህ። (የሚቀጥለው ከግሪክ የተጨመረ ነው።) ልጄ ለራስህ አዋቂ ብትሆን ለባልንጀራህም አዋቂ ትሆናለህ፥ ለራስህ ክፉ ብትሆን ግን ክፋትን ለብቻህ ትሸከማለህ። ሐሰትን የሚያዘጋጅ ሰው ነፋሳትን እንደሚገዛ ነው፥ የሚበርር ወፍንም እንደሚከተል ይመስላል። የወይኑ ቦታ መንገዱን ረስቷልና፥ የሚሠማራባትን መንገድ እንዲስት አድርጓልና፥ ወደ ምድረ በዳ ይሄዳል፥ ለጥም ወደ ተሠራች አገር ይሄዳል፥ የማያፈራ የማይጠቅም ገንዘብንም በእጁ ይሰበስባል።