ኢዮብ 21:17 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)17 “የክፉዎች መብራት የጠፋው፥ መቅሠፍትም የመጣባቸው፥ እግዚአብሔርም በቁጣው መከራ የከፈላቸው፥ ምዕራፉን ተመልከትአዲሱ መደበኛ ትርጒም17 “የኀጢአተኞች መብራት የጠፋው ስንት ጊዜ ነው? የእግዚአብሔር ቍጣ መከራ የመጣባቸው፣ መቅሠፍትም የደረሰባቸው ስንት ጊዜ ነው? ምዕራፉን ተመልከትአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም17 “ለመሆኑ የክፉ ሰዎች መብራት ጠፍቶ ያውቃልን? መቅሠፍትስ በእነርሱ ላይ ወርዶ ያውቃልን? እግዚአብሔር በቊጣው ቀጥቶአቸው ያውቃልን? ምዕራፉን ተመልከትየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)17 የኃጥኣን መብራት ትጠፋለች፤ መቅሠፍትም ትመጣባቸዋለች። የበቀል ቍጣም ይይዛቸዋል፤ ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)17 የኃጥአን መብራት የጠፋው፥ መቅሠፍትም የመጣባቸው፥ እግዚአብሔርም በቍጣው መከራ የከፈላቸው፥ ምዕራፉን ተመልከት |