Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ኢዮብ 13:4 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

4 እናንተ ግን በሐሰት ለባጮች ናችሁ፥ ሁላችሁም የማትጠቅሙ ሐኪሞች ናችሁ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

4 እናንተ ግን፣ በሐሰት የምትለብጡ ናችሁ፤ ሁላችሁ የማትረቡ ሐኪሞች ሆናችኋል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

4 እናንተ ግን በሐሰት የተሞላችሁ ናችሁ፤ ማንንም መፈወስ እንደማይችሉ ሐኪሞች ናችሁ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

4 እና​ንተ ግን የዐ​መፅ ባለ መድ​ኀ​ኒ​ቶች፥ ሁላ​ች​ሁም የክ​ፋት ፈዋ​ሾች ናችሁ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

4 እናንተ ግን በሐሰት ለባጮች ናችሁ፥ ሁላችሁ የማትጠቅሙ ባለ መድኃኒቶች ናችሁ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ኢዮብ 13:4
23 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

እኔም እንዲህ ብዬ ላክሁበት፦ “አንተ ከምትለው ነገር አንድም አልተደረገም፥ አንተ ከልብህ ፈጥረኸዋልና”


“እንደዚህ ያለ ነገር አብዝቼ ሰማሁ፥ እናንተ ሁላችሁ የምታደክሙ አጽናኞች ናችሁ።


እነሆ፥ ሁላችሁም አይታችኋል፥ ታዲያ ለምን በከንቱ ትባክናላችሁ?”


ወንድሞቼ እንደ ፈፋ፥ እንደሚያልፍ ፈፋ ሐሰተኞች ሆኑብኝ።


ተስፋ አድርገውባቸው ነበርና አፈሩ፥ ወደዚያ ደረሱ፥ እፍረትም ያዛቸው።


አሁንም እናንተ እንደዚሁ ሆናችኋል፥ መከራዬን አይታችሁ ፈራችሁ።


የትዕቢተኞች ዓመጽ በላዬ በዛ፥ እኔ ግን በፍጹም ልቤ ትእዛዛትህን እፈልጋለሁ።


“በባልንጀራህ ላይ በሐሰት አትመስክር።


እነሆ፥ ሐሰትን ትንቢት በሚያልሙ በሚናገሩም፥ በሐሰታቸውና በድፍረታቸውም ሕዝቤን በሚያስቱ በነቢያት ላይ ነኝ፥ ይላል ጌታ፤ እኔም አልላክኋቸውም አላዘዝኋቸውምም፥ ለእነዚህም ሕዝብ በማናቸውም ነገር አይጠቅሙአቸውም፥ ይላል ጌታ።


ሙግትህን የሚፈርድልህ የለም፥ ለቁስልህም መድኃኒት የለውም፥ ለአንተም ፈውስ የለህም።


ድንግሊቱ የግብጽ ልጅ ሆይ! ወደ ገለዓድ ውጪ የሚቀባንም መድኃኒት ውሰጂ፤ ብዙ መድኃኒቶችን የተጠቀምሺው በከንቱ ነው፤ ለአንቺ መዳኛ የለሽም።


የሕዝቤንም ስብራት በጥቂቱ ይፈውሳሉ፤ ሰላም ሳይሆን፦ ‘ሰላም ሰላም’ ይላሉ።


በገለዓድ የሚቀባ መድኃኒት የለምን? ወይስ በዚያ ሐኪም የለምን? የወገኔ ሴት ልጅ ፈውስ ስለምን አልሆነም?


የደከሙትን አላበረታችሁም፥ የታመመውን አላከማችሁትም፥ የተሰበረውን አልጠገናችሁትም፥ የባዘነውን አልመለሳችሁትም፥ የጠፋውንም አልፈለጋችሁትም በኃይልና በጭቆና ገዛችኋቸው።


ኤፍሬምም ደዌውን፥ ይሁዳም ቁስሉን ባየ ጊዜ ኤፍሬም ወደ አሦር ሄደ፥ ወደ ታላቁም ንጉሥ መልእክተኛን ላከ፤ እርሱ ግን ሊፈውሳችሁ፥ ከቁስላችሁም ሊያድናችሁ አልቻለም።


ኢየሱስም ሰምቶ “ሕመምተኞች እንጂ ጤነኞች ባለ መድኃኒት አያስፈልጋቸውም፤ ኀጢአተኞችን እንጂ ጻድቃንን ልጠራ አልመጣሁም፤” አላቸው።


በብዙ ባለ መድኀኒቶችም ዘንድ ብዙ ተሠቃይታ፥ ያላትን ሁሉ ጨረሰች እንጂ አልተሻላትም ነበር፤ እንዲያውም ሕመሙ ብሶባት ነበር።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች