ኢዮብ 11:6 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)6 የጥበቡን ምሥጢር ቢገልጥልህ! ማስተዋሉ እጥፍ ነውና። እግዚአብሔር ለበደልህ ከሚገባው አሳንሶ እንደሚያስከፍልህ እወቅ።” ምዕራፉን ተመልከትአዲሱ መደበኛ ትርጒም6 ትክክለኛ ጥበብ ባለብዙ ፈርጅ ናትና፣ የጥበብንም ምስጢር ምነው በገለጠልህ! እግዚአብሔር ለኀጢአትህ የሚገባውን እንዳላስከፈለህ ባወቅህ ነበር። ምዕራፉን ተመልከትአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም6 የጥበብ መንገድ ብዙ ስለ ሆነ፥ ምነው ጌታ የጥበብን ምሥጢር ቢገልጥልህ! ስለዚህ እግዚአብሔር የቀጣህ፥ ከሚገባህ አሳንሶ መሆኑን ዕወቅ። ምዕራፉን ተመልከትየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)6 የጥበቡን ኀይል ቢገልጥልህ! ባንተ ላይ ያለው እጥፍ ነውና። ያንጊዜም ከእግዚአብሔር ዘንድ በበደልህ ያገኘህ ትክክል እንደ ሆነ ታውቃለህ። ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)6 የጥበቡን ምሥጢር ቢገልጥልህ! ማስተዋሉ ብዙ ነውና። እግዚአብሔር ለበደልህ ከሚገባው አሳንሶ እንደሚያስከፍልህ እወቅ። ምዕራፉን ተመልከት |