ኢዮብ 1:3 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)3 ሰባት ሺህ በጎች፥ ሦስት ሺህ ግመሎች፥ አምስት መቶ ጥማድ በሬዎች፥ አምስት መቶ እንስት አህዮችና እጅግ ብዙም አገልጋዮች ነበሩት። ያም ሰው በምሥራቅ ካሉ ሰዎች ሁሉ ይልቅ ታላቅ ነበረ። ምዕራፉን ተመልከትአዲሱ መደበኛ ትርጒም3 ሀብቱም ሰባት ሺሕ በጎች፣ ሦስት ሺሕ ግመሎች፣ ዐምስት መቶ ጥማድ በሬዎችና ዐምስት መቶ እንስት አህዮች ነበረ፤ እጅግ ብዙ ባሮችም ነበሩት፤ በምሥራቅ አገር ከሚኖሩትም ሰዎች ሁሉ ይልቅ እጅግ ታላቅ ሰው ነበረ። ምዕራፉን ተመልከትአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም3 በሀብትም በኩል ሰባት ሺህ በጎች፥ ሦስት ሺህ ግመሎች፥ አምስት መቶ ጥማድ በሬዎችና አምስት መቶ አህዮች ነበሩት፤ እንዲሁም እጅግ ብዙ አገልጋዮች ነበሩት፤ በምሥራቅ አገር ካሉት ሰዎች ሁሉ እርሱን የሚያኽል ሀብታምና ታላቅ ሰው አልነበረም። ምዕራፉን ተመልከትየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)3 ከብቶቹም፦ ሰባት ሺህ በጎች፥ ሦስት ሺህ ግመሎች፥ አምስት መቶም ጥማድ በሬ፥ አምስት መቶም እንስት አህዮች ነበሩ፤ እጅግ ብዙም አገልጋዮች ነበሩት፤ ሥራውም በምድር ላይ ታላቅ ነበረ፤ ያም ሰው በምሥራቅ ካሉ ሰዎች ሁሉ ይልቅ ገናና ነበረ። ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)3 ሀብቱም ሰባት ሺህ በጎች፥ ሦስት ሺህም ግመሎች፥ አምስት መቶም ጥማድ በሬ፥ አምስት መቶም እንስት አህዮች ነበረ፥ እጅግ ብዙም ባሪያዎች ነበሩት፥ ያም ሰው በምሥራቅ ካሉ ሰዎች ሁሉ ይልቅ ታላቅ ነበረ። ምዕራፉን ተመልከት |