Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ኤርምያስ 9:13 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

13 ጌታም እንዲህ አለ፦ “የሰጠኋቸውን ሕጌን ትተዋልና፥ ድምፄንም አልሰሙምና፥ በእርሱም አልተመላለሱምና፥

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

13 እግዚአብሔርም እንዲህ አለ፤ “ይህ የሆነው የሰጠኋቸውን ሕጌን ትተው ስላልታዘዙኝና ሥርዐቴን ስላልተከተሉ ነው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

13 እግዚአብሔርም እንዲህ ሲል መለሰ፦ “ይህ ሁሉ ሊሆን የቻለው ሕዝቤ እኔ የሰጠኋቸውን ሕግ በመተዋቸው ነው፤ እነርሱ ለእኔ አልታዘዙም፤ የነገርኳቸውንም ሁሉ አልፈጸሙም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

13 እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም እን​ዲህ አለኝ፦ ሕዝቤ በፊ​ታ​ቸው የሰ​ጠ​ኋ​ቸ​ውን ሕጌን ትተ​ዋል፤ ቃሌ​ንም አል​ሰ​ሙም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

13 እግዚአብሔርም እንዲህ አለ፦ የሰጠኋቸውን ሕጌን ትተዋልና፥ ቃሌንም አልሰሙምና፥

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ኤርምያስ 9:13
11 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

“እናንተ ግን እኔን ከመከተል ብትመለሱ፥ የሰጠኋችሁንም ሥርዓቴንና ትእዛዜን ብትተዉ፥ ሄዳችሁም ሌሎችን አማልክት ብታመልኩ ብትሰግዱላቸውም፥


ስለዚህ አምላካችን ሆይ ከዚህ በኋላ ምን እንላለን? ትእዛዛትህን ትተናልና፤


ሕግህን ከተዉ ከኃጢአተኞች የተነሣ ኀዘን ያዘኝ።


ሕግን የሚተዉ ሰዎች ክፉዎችን ያመሰግናሉ፥ ሕግ ጠባቂዎች ግን ይቃወሟቸዋል።


ቃሌን ለመስማት እንቢ የሚሉ፥ በልባቸውም እልከኝነት የሚሄዱ፥ ሊያገለግሉአቸውና ሊሰግዱላቸው ሌሎችን አማልክት የሚከተሉ፥ እነዚህ ክፉ ሕዝብ አንዳች እንደማይረባ እንደዚህ መታጠቂያ ይሆናሉ።


እነርሱም፦ “የአምላካቸውን የጌታን ቃል ኪዳን ትተው ለሌሎች አማልክት ስለ ሰገዱ ስላገለገሉአቸውም ነዋ ብለው ይመልሳሉ።”


እንዲህም ይሆናል፤ እናንተ፦ “አምላካችን ጌታ እነዚህን ነገሮች ሁሉ ለምን አደረገብን?” ቢሉ፥ አንተ፦ “እንደ ተዋችሁኝ፥ በአገራችሁም ሌሎችን አማልክት እንዳገለገላችሁ፥ እንዲሁ ለእናንተ ባልሆነ አገር ለሌሎች ሰዎች ታገለግላላችሁ” ትላቸዋለህ።


ነገር ግን አንገታቸውን አደነደኑ እንጂ አልሰሙኝም ጆሮአቸውንም አላዘነበሉም፤ አባቶቻቸውም ካደረጉት ይልቅ የባሰ አደረጉ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች