Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ኤርምያስ 8:11 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

11 የሕዝቤንም ሴት ልጅ ስብራት በጥቂቱ ይፈውሳሉ፤ ሰላም ሳይሆን፦ ‘ስለም ሰላም’ ይላሉ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

11 የሕዝቤን ቍስል ብርቱ እንዳይደለ በመቍጠር፣ የተሟላ ፈውስ ሳይኖር እንዲሁ ያክማሉ፤ ሰላም ሳይኖር፣ “ሰላም፣ ሰላም” ይላሉ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

11 የሕዝቤንም የስብራት ቊስል እንደ ቡጭራት በመቊጠር በሚገባ አያክሙትም፤ እንዲሁም ሰላም ሳይኖር ‘ሰላም ነው ሰላም ነው’ ይላሉ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

11 የሕ​ዝ​ቤ​ንም ሴት ልጅ ስብ​ራት በማ​ቃ​ለል ይፈ​ው​ሳሉ፤ ሰላም ሳይ​ሆን፦ ሰላም ሰላም ይላሉ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

11 የሕዝቤንም ሴት ልጅ ስብራት በጥቂቱ ይፈውሳሉ፥ ሰላም ሳይሆን፦ ስለም ሰላም ይላሉ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ኤርምያስ 8:11
14 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ሚክያስን ለመጥራት ሄዶ የነበረው መልእክተኛ በዚሁ ጊዜ ሚክያስን “ሌሎቹ ነቢያት በሙሉ ንጉሥ አክዓብ ድል የሚያደርግ መሆኑን የሚያረጋግጥ የትንቢት ቃል ተናግረዋል፤ ስለዚህም አንተም እንደ እነርሱ ብታደርግ ይሻልሃል” አለው።


ስለዚህ አክዓብ አራት መቶ የሚሆኑትን ነቢያቱን ጠርቶ “ወደ ራሞት ሄጄ አደጋ ልጣልባት ወይስ ልተው?” ሲል ጠየቃቸው። እነርሱም “ሄደህ አደጋ ጣልባት፤ ጌታም ድልን ያቀዳጅሃል” ሲሉ መለሱለት።


እኔም፦ “ጌታ እግዚአብሔር ሆይ! ወዮ! እነሆ፥ ነቢያት፦ ‘ዘላቂ ሰላም በዚህ ስፍራ እሰጣችኋለሁ እንጂ ሰይፍን አታዩም፥ ራብም አያገኛችሁም’ ይሉአቸዋል” አልሁ።


ለሚንቁኝ ሁልጊዜ፦ ጌታ፦ ሰላም ይሆንላችኋል ብሏል ይላሉ፤ በልቡም እልከኝነት ለሚሄድ ሁሉ፦ ክፉ ነገር አያገኛችሁም ይላሉ።


የሕዝቤንም ስብራት በጥቂቱ ይፈውሳሉ፤ ሰላም ሳይሆን፦ ‘ሰላም ሰላም’ ይላሉ።


ሰላምን በተስፋ ተጠባበቅን፥ መልካምም አልተገኘም፤ መፈወስን በተስፋ ተጠባበቅን፥ እነሆም፥ ድንጋጤ ሆነ።


ኖን። ነቢዮችሽ ከንቱና ሐሰተኛ ራእይ አይተውልሻል፥ ምርኮሽንም ይመልሱ ዘንድ በደልሽን አልገለጡም፥ ከንቱና የማይረባ ነገርንም አይተውልሻል።


ምክንያቱም እኔ ያላሳዘንሁትን የጻድቁን ልብ በውሸት አሳዝናችኋልና፥ ከክፉ መንገዱ ተመልሶ በሕይወትም እንዳይኖር የኃጢአተኛውን እጅ አበርትታችኋልና፤


በነፋስና በውሸት የሚሄድ፥ ሐሰትንም የሚናገር፥ “ስለ ወይን ጠጅና ስለሚያሰክር መጠጥ ስብከት እናገርልሃለሁ” የሚል ሰው ቢኖር፥ እርሱ የዚህ ሕዝብ ሰባኪ ይሆናል።


እነርሱም፦ “ሰላምና ደኅንነት ነው” በሚሉ ጊዜ ምጥ እንደ ያዛት እርጉዝ ሴት ድንገተኛ ጥፋት በእነርሱ ላይ ይመጣባቸዋል፤ ከቶም አያመልጡም።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች