ኤርምያስ 52:21 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)21 እነዚህም ዓምዶች፥ የአንዱ ዓምድ ቁመት ዐሥራ ስምንት ክንድ ነበረ፥ የዙሪያውም ልኬት ዐሥራ ሁለት ክንድ ነበረ፤ ውፍረቱም አራት የጣት ስንዝር ያህል ነበረ፥ መሀል ለመሀልም ክፍት ነበረ። ምዕራፉን ተመልከትአዲሱ መደበኛ ትርጒም21 እያንዳንዱም ዐምድ ከፍታው ዐሥራ ስምንት ክንድ ዙሪያ ክቡም ዐሥራ ሁለት ክንድ ነበረ፤ ውስጡ ክፍት ስለ ሆነ የእያንዳንዱ ከንፈር ውፍረት አራት ጣት ነበረ። ምዕራፉን ተመልከትአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም21 ሁለቱ ዐምዶች አንድ ዐይነት ቅርጽ ያላቸው ሆነው እያንዳንዳቸው ስምንት ሜትር ቁመትና አምስት ሜትር የሚያኽል ዙሪያ ነበራቸው፤ ውስጣቸውም ክፍት ነበር፤ ብረቱም ሰባ አምስት ሚሊ ሜትር ውፍረት ነበረው፤ ምዕራፉን ተመልከትየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)21 ዐምዶቹም፥ የአንዱ ዓምድ ቁመት ዐሥራ ስምንት ክንድ ነበረ፥ የዙሪያውም መጠን ዐሥራ ሁለት ክንድ ነበረ፤ ውፍረቱም ጋት ያህል ነበረ፤ ባዶም ነበረ። ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)21 ዓምዶቹም፥ የአንዱ ዓምድ ቁመት አሥራ ስምንት ክንድ ነበረ፥ የዙሪያውም መጠን አሥራ ሁለት ክንድ ነበረ፥ ውፍረቱም አራት ጣት ያህል ነበረ፥ ባዶም ነበረ። ምዕራፉን ተመልከት |