ኤርምያስ 51:64 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)64 አንተም እንዲህ በል፦ ‘እኔ ከማመጣባት ክፉ ነገር የተነሣ እንዲሁ ባቢሎን ትሰጥማለች አትነሣምም።’ ” የኤርምያስ ቃላት እስከዚህ ድረስ ነው። ምዕራፉን ተመልከትአዲሱ መደበኛ ትርጒም64 እንዲህም በል፤ ‘ባቢሎንም እኔ ከማመጣባት ጥፋት የተነሣ፣ እንደዚሁ ትሰጥማለች፤ ከእንግዲህም አትነሣም፤ ሕዝቧም ይወድቃል።’ ” የኤርምያስ ትንቢት እዚህ ላይ አበቃ። ምዕራፉን ተመልከትአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም64 እንዲህም በል፦ ‘ባቢሎንም እንደዚሁ እግዚአብሔር በእርስዋ ላይ ከሚያመጣው ጥፋት የተነሣ ወድቃ ትቀራለች እንጂ እንደገና መነሣት አትችልም።’ ” ኤርምያስ የተናገረው ቃል እዚህ ላየ ተፈጸመ። ምዕራፉን ተመልከትየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)64 አንተም፦ እኔ ከማመጣባት ክፉ ነገር የተነሣ እንዲሁ ባቢሎን ትሰጥማለች፤ አትነሣምም በል።” የኤርምያስ ቃል እስከዚህ ድረስ ነው። ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)64 አንተም፦ እኔ ከማመጣባት ክፉ ነገር የተነሣ እንዲሁ ባቢሎን ትሰጥማለች አትነሣምም በል። የኤርምያስ ቃል እስከዚህ ድረስ ነው። ምዕራፉን ተመልከት |