Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ኤርምያስ 51:47 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

47 ስለዚህ፥ እነሆ፥ የተቀረጹትን የባቢሎን ምስሎች የምቀጣበት ዘመን ይመጣል፥ ምድርዋም ሁሉ ያፈረች ትሆናለች ተወግተውም የሞቱት ሁሉ በመካከልዋ ይወድቃሉ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

47 የባቢሎንን ጣዖታት የምቀጣበት ጊዜ፣ በርግጥ ይመጣልና። ምድሯ በሙሉ ትዋረዳለች፤ የታረዱትም በሙሉ በውስጧ ይወድቃሉ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

47 ስለዚህም የባቢሎንን ጣዖቶች የማስወግድበት ጊዜ ይመጣል፤ በምድሪቱ ሁሉ ላይ ኀፍረት ይደርሳል፤ የተገደሉባት ልጆችዋ ሁሉ በመካከልዋ ይወድቃሉ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

47 ስለ​ዚህ እነሆ የተ​ቀ​ረ​ጹ​ትን የባ​ቢ​ሎ​ንን ምስ​ሎች የም​በ​ቀ​ል​በት ዘመን ይመ​ጣል፤ ምድ​ር​ዋም ሁሉ ትደ​ር​ቃ​ለች፤ ተዋ​ግ​ተ​ውም የሞ​ቱት ሁሉ በመ​ካ​ከ​ልዋ ይወ​ድ​ቃሉ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

47 ስለዚህ፥ እነሆ፥ የተቀረጹትን የባቢሎን ምስሎች የምቀጣበት ዘመን ይመጣል፥ ምድርዋም ሁሉ ታፍራለች፥ ተወግተውም የሞቱት ሁሉ በመካከልዋ ይወድቃሉ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ኤርምያስ 51:47
13 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

እነሆም፥ በፈረሶች የሚቀመጡ፥ ሁለት ሁለት ሁነው የሚሄዱ ፈረሰኞች ይመጣሉ ብሎ ጮኸ፤ እርሱም መልሶ፦ ባቢሎን ወደቀች ወደቀች፥ የተቀረጹም የአማልክቶችዋ ምስሎች ሁሉ በምድር ላይ ተጥለው ደቀቁ አለ።


የሠራዊት ጌታ እንዲህ ይላል፦ እነሆ፥ እቀጣቸዋለሁ፤ ጉልማሶቻቸው በሰይፍ ይሞታሉ፥ ወንዶችና ሴቶች ልጆቻቸውም በራብ ይሞታሉ፤


ወዳጆችሽ እንዲሆኑ ያስተማርሻቸውን በራስሽ ላይ አለቆች ባደረጋቸው ጊዜ ምን ትያለሽ? እንደ ወላድ ሴት ምጥ አይዝሽምን?


ነቢይና ካህን ሕዝቡም ‘የጌታ ሸክም’ ብሎ ቢናገር፥ ያን ሰውና ቤቱን እቀጣለሁ።


ሰባው ዓመትም በተፈጸመ ጊዜ፥ የባቢሎንን ንጉሥና ያንን ሕዝብ ስለ ኃጢአታቸው እቀጣለሁ፥ ይላል ጌታ፥ የከለዳውያንንም ምድር ለዘለዓለም ባድማ አደርጋታለሁ።


በአሕዛብ መካከል ተናገሩ አውጁም፥ ዓላማውንም አንሡ፤ አውጁ፥ ሳትደብቁም እንዲህ በሉ፦ ባቢሎን ተያዘች፥ ቤል አፈረ፥ ሜሮዳክ ተሰባበረ፤ ምስሎችዋ አፈሩ፥ ጣዖታትዋ ተሰባበሩ።


እነርሱ ምናምንቴና የቀልድ ሥራ ናቸው፤ በተጐበኙ ጊዜ ይጠፋሉ።


በጽዮን በዓይናችሁ ፊት ስለ ሠሩት ክፋታቸው ሁሉ በባቢሎንና በከለዳውያን ምድር በሚኖሩ ሁሉ ላይ ፍዳቸውን እከፍላለሁ፥ ይላል ጌታ።


ከተሞችዋ ባድማና ደረቅ ምድር ምድረ በዳም፥ ሰውም የማይቀመጥባቸው የሰውም ልጅ የማያልፍባቸው ምድር ሆኑ።


ስለዚህ፥ እነሆ፥ የተቀረጹትን ምስሎችዋን የምቀጣበት በምድርዋም ላይ ሁሉ የተወጋው የሚያቃስትበት ዘመን ይመጣል፥ ይላል ጌታ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች