Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ኤርምያስ 51:43 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

43 ከተሞችዋ ባድማና ደረቅ ምድር ምድረ በዳም፥ ሰውም የማይቀመጥባቸው የሰውም ልጅ የማያልፍባቸው ምድር ሆኑ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

43 ከተሞቿ ሰው የማይኖርባቸው፣ ዝርም የማይልባቸው፣ ደረቅና ምድረ በዳ፣ ባድማ ምድርም ይሆናሉ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

43 ከተሞቹ ውሃ የማይገኝባቸውና ማንም ሊኖርባቸውም ሆነ ሊተላለፍባቸው የማይችል ምድረ በዳ ሆነዋል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

43 ከተ​ሞ​ችዋ ባድ​ማና ደረቅ ምድር፥ ሰውም የማ​ይ​ቀ​መ​ጥ​በት፥ የሰ​ውም ልጅ የማ​ያ​ል​ፍ​በት ምድር ሆኑ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

43 ከተሞችዋ ባድማና ደረቅ ምድር ምድረ በዳም፥ ሰውም የማይቀመጥበት የሰውም ልጅ የማያልፍበት ምድር ሆኑ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ኤርምያስ 51:43
12 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

እነርሱም፦ ‘ከግብጽ ምድር ያወጣን፥ በምድረ በዳም በባድማ ጉድጓድም ባለበት ምድር፥ በውኃ ጥምና በሞት ጥላ ምድር፥ ማንም በማያልፍበትና ማንም በማይቀመጥበት ምድር የመራን ጌታ ወዴት አለ?’ አላሉም።


በዘመናት ሁሉ የሚቀመጥባት አይኖርም፤ የሚቀመጥባትም የለም ዐረብ በዚያ ድንኳኑን አይተክልም፤ እረኛም መንጋውን በዚያ አያሳርፍም።


ማንም እንዳይቀመጥባት የባቢሎንን ምድር ባድማ ለማድረግ የጌታ አሳብ በባቢሎን ላይ ጸንቶአልና ምድር ተናወጠች ተወራጨችም።


ባቢሎንም የፍርስራሽ ክምር፥ የቀበሮ ማደሪያ ሰውም የማይቀመጥባት መሣቀቅያና ማፍዋጫ ትሆናለች።


እናታችሁ እጅግ ታፍራለች፥ የወለደቻችሁም ትዋረዳለች፤ እነሆ፥ በአሕዛብ መካከል ኋለኛይቱ ትሆናለች፤ ምድረ በዳና ደረቅ ምድር በረሀም ትሆናለች።


የሠራዊት ጌታ ከእኛ ጋር ነው፥ የያዕቆብ አምላክ መጠጊያችን ነው።


በዚህ ምክንያት ክፉ ነገር ይመጣብሻል፥ በምዋርትሽም እንዴት እንደምታርቂው አታውቂም፤ ጉዳት ይወድቅብሻል ልታስወግጂውም አትችይም፤ የማታውቂያትም ጉስቁልና ድንገት ትመጣብሻለች።


እንዲህ በል፦ ‘አቤቱ፥ ከሰው ጀምሮ እስከ እንስሳ ድረስ ማንም እንዳይቀመጥባት፥ ለዘለዓለምም ባድማ እንድትሆን ልታጠፋት በዚህች ስፍራ ላይ አንተ ተናግረሃል።’


በአዳራሾችዋም እሾህ፥ በቅጥሮችዋም ሳማና አሜከላ ይበቅሉባታል፤ የቀበሮም ማደሪያና የሰጎን ሥፍራ ትሆናለች።


ምድራቸውን ለመሣቀቂያና ለዘለዓለም ማፍዋጫ አድርገዋል፤ የሚያልፍባት ሁሉ ይደነቃል፥ ራሱንም ይነቀንቃል።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች