Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ኤርምያስ 51:36 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

36 ስለዚህ ጌታ እንዲህ ይላል፦ እነሆ፥ ሙግትሽን እምዋገትልሻለሁ በቀልሽንም እበቀልልሻለሁ፤ ባሕርዋንም አደርቀዋለሁ ምንጭዋንም እንዲደርቅ አደርጋለሁ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

36 ስለዚህ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “እነሆ፤ እሟገትልሻለሁ፣ በቀልሽንም እኔ እበቀልልሻለሁ፤ ባሕሯን አደርቃለሁ፣ የምንጮቿንም ውሃ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

36 ስለዚህ እግዚአብሔር ለኢየሩሳሌም ሕዝብ እንዲህ ይላል፦ “እኔ እናንተን እረዳለሁ፤ ባቢሎናውያንንም እበቀልላችኋለሁ፤ የባቢሎን የውሃ ምንጭና ወንዞችዋ ሁሉ እንዲደርቁ አደርጋለሁ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

36 ስለ​ዚህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፥ “እነሆ የሚ​ገ​ፋ​ሽን እፈ​ር​ድ​በ​ታ​ለሁ፤ በቀ​ል​ሽ​ንም እበ​ቀ​ል​ል​ሻ​ለሁ፤ ባሕ​ር​ዋ​ንም ድርቅ አደ​ር​ገ​ዋ​ለሁ፤ ምን​ጭ​ዋ​ንም አደ​ር​ቃ​ለሁ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

36 ስለዚህ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እነሆ፥ እምዋገትልሻለሁ በቀልሽንም እበቀልልሻለሁ፥ ባሕርዋንም ድርቅ አደርገዋለሁ ምንጭዋንም አደርቀዋለሁ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ኤርምያስ 51:36
24 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

“በቀል የእኔ ነው፤ እኔ ብድራቱን እመልሳለሁ፤ ይላል ጌታ” ተብሎ ተጽፎአልና፥ ተወዳጆች ሆይ! ራሳችሁ አትበቀሉ፤ ለቁጣው ቦታ ስጡ እንጂ።


እርሷ የተቀረጹ ምስሎች ምድር ናትና፥ እነርሱም በጣዖታቱ ላይ እንደ እብድ ይሆናሉና ድርቅ በውኆችዋ ላይ ይሆናል እነርሱም ይደርቃሉ።


ተናጋሪ ሰው በምድር ውስጥ አይጸናም፥ ዓመፀኛን ሰው ክፋት ለጥፋት ይፈልገዋል።


ቀላዩም፦ “ደረቅ ሁን፥ ፈሳሾችህንም አደርቃለሁ” እላለሁ፤


“የአገልጋዮቹን ደም ይበቀላልና፥ ጠላቶቹንም ይበቀላቸዋልና፥ ምድሪቱንና ሕዝቡን ይክሳልና፥ እናንተ አሕዛብ ሆይ፥ ከሕዝቡ ጋር ደስ ይበላችሁ።”


በቀልና ብድራት መመለስ የእኔ ነው፤ እግራቸው የሚሰናከልበት ጊዜው፥ የመጥፊያቸው ቀን ቀርቧልና፥ የሚመጣባቸው ፍርድ ይፈጥናል።


ስድስተኛውም መልአክ ጽዋውን በታላቁ ወንዝ በኤፍራጥስ ላይ አፈሰሰ፤ ከፀሐይም መውጫ ለሚመጡ ነገሥታት መንገድ እንዲሰናዳላቸው ውሃው ደረቀ።


ከባቢሎን ውስጥ ሽሹ፥ እያንዳንዳችሁም ነፍሳችሁን አድኑ፤ በበደልዋ አትጥፉ፥ የጌታ የበቀል ጊዜ በእርሷ ላይ ነውና፥ እርሱም ብድራትዋን ይከፍላታልና።


የእስራኤል ቅዱስ፥ የሚቤዣችሁ፥ ጌታ እንዲህ ይላል፦ ስለ እናንተ ወደ ባቢሎን ሰድጃለሁ፥ ከላዳውያንንም ሁሉ ስደተኞች አድርጌ በሚመኩባቸው መርከቦች አዋርዳቸዋለሁ።


ታዳጊአቸው ኃያል ነውና፥ እርሱም ፍርዳቸውን ከአንተ ጋር ይፋረዳልና።


ምክንያቱም ጌታ ለእነርሱ ይሟገታልና፥ የቀሙአቸውንም ሰዎች ሕይወት ይቀማልና።


ወንዞችን ምድረ በዳ፥ የውኃውንም ምንጮች ደረቅ መሬት አደረገው፥


የዐባይ ወንዝ ይጎድላል፤ ወንዙም እያነሰም ይሄዳል ደረቅም ይሆናል።


ፍላጾችን ሳሉ ጋሻዎችንም አንሡ፤ ጌታ ሊያጠፋት አሳቡ በባቢሎን ላይ ነውና የሜዶንን ነገሥታት መንፈስ አስነሥቶአል፤ የጌታ በቀል ስለ መቅደሱ ሲል የሚበቀለው በቀል በእርሷ ላይ ነውና።


በወንድሞቹ መካከል ፍሬያማ ቢሆንም እንኳ የምሥራቅ ነፋስ ይመጣል፥ የጌታ ነፋስ ከምድረበዳ ይመጣል፤ ፈሳሹንም ይጠፋል፥ ምንጩንም ይደርቃል፥ የተከበሩ ዕቃዎች ሁሉ ያሉበትን መዝገብ ይበዘብዛል።


በሕዝቤ በእስራኤል እጅ ኤዶምን እበቀላለሁ፤ እንደ ቁጣዬና እንደ መዓቴ መጠን በኤዶም ላይ ያደርጋሉ፤ በቀሌንም ያውቃሉ፤ ይላል ጌታ እግዚአብሔር።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች