ኤርምያስ 51:23 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)23 በአንቺም እረኛውንና መንጋውን እሰባብራለሁ፤ በአንቺም አራሹንና ጥማጁን እሰባብራለሁ፤ በአንቺም ገዢዎችንና ሹማምቶችን አሰባብራለሁ። ምዕራፉን ተመልከትአዲሱ መደበኛ ትርጒም23 በአንቺ እረኛውንና መንጋውን እሰባብራለሁ፣ በአንቺ ገበሬውንና በሬውን እሰባብራለሁ፤ በአንቺ ገዦችንና ባለሥልጣኖችን እሰባብራለሁ። ምዕራፉን ተመልከትአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም23 እረኛውንና መንጋውን፥ ገበሬውንና ጥማድ በሬዎቹን፥ ገዢዎችንና ታላላቅ ባለሥልጣኖችን ለማጥፋት መሣሪያ አደረግሁሽ።” ምዕራፉን ተመልከትየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)23 በአንቺም እረኛውንና መንጋውን እበትናለሁ፤ በአንቺም አራሹንና ጥማዱን እበትናለሁ፤ በአንቺም አለቆችንና መሳፍንትን እበትናለሁ። ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)23 በአንቺም እረኛውንና መንጋውን እሰባብራለሁ፥ በአንቺም አራሹንና ጥማጁን እሰባብራለሁ፥ በአንቺም አለቆችንና ሹማምቶችን አሰባብራለሁ። ምዕራፉን ተመልከት |