Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ኤርምያስ 50:44 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

44 እነሆ፥ በጽኑ የበጎች በረት ላይ ከዮርዳኖስ ዱር ውስጥ እንደሚወጣ አንበሳ እንዲሁ እኔ ከእርሷ ዘንድ በድንገት አባርራቸዋለሁ፤ የተመረጠውንም ማንኛውንም ሰው በእርሷ ላይ እሾመዋለሁ፤ እንደ እኔ ያለ ማን ነው? ወይስ እኔን እንድመጣ የሚጠራኝ ማን ነው? ወይስ በፊቴ የሚቆም እረኛ ማን ነው?

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

44 አንበሳ ከዮርዳኖስ ደኖች ድንገት ወጥቶ፣ ወደ ግጦሽ ሜዳ ብቅ እንደሚል፣ እኔም ባቢሎንን ሳይታሰብ ከምድሯ አባርራታለሁ፤ የመረጥሁትንም በርሷ ላይ እሾማለሁ፤ እንደ እኔ ያለ ማን ነው? ማንስ ሊገዳደረኝ ይችላል? የትኛውስ እረኛ ሊቋቋመኝ ይችላል?”

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

44 “በዮርዳኖስ ወንዝ ዳርቻ ከሚገኘው ጥቅጥቅ ካለ ደን ወደ ለምለም መስክ እንደሚወጣ አንበሳ፥ እኔ እግዚአብሔር መጥቼ ባቢሎናውያን ድንገት ከከተማቸው ወጥተው እንዲባረሩ አደርጋለሁ፤ ከዚያም በኋላ እኔ የምመርጠውን እሾማለሁ፤ ታዲያ እንደ እኔ ያለ ማን ነው? ሊጠይቀኝ የሚደፍር ማነው? የሚቋቋመኝስ መሪ ማን ነው?

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

44 እነሆ ከእ​ር​ስዋ ዘንድ በቶሎ አባ​ር​ራ​ቸ​ዋ​ለ​ሁና እንደ አን​በሳ ከዮ​ር​ዳ​ኖስ ዳር ወደ ኤታም ምድር ይወ​ጣል፤ ጐል​ማ​ሶ​ቹ​ንም ሁሉ በእ​ር​ስዋ ላይ እሾ​ማ​ለሁ፤ እንደ እኔ ያለ ማን ነው? ወይስ ለእኔ ጊዜን የሚ​ወ​ስን ማን ነው? ወይስ ፊቴን የሚ​ቋ​ቋም እረኛ ማን ነው?

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

44 እነሆ፥ ከእርስዋ ዘንድ በቶሎ አባርራቸዋለሁና በጠነከረው አምባ ላይ ከዮርዳኖስ ትዕቢት ውስጥ እንደ አንበሳ ይወጣል፥ የተመረጠውንም በእርስዋ ላይ እሾመዋለሁ፥ እንደ እኔ ያለ ማን ነው? ወይስ ለእኔ ጊዜ የሚወስን ማን ነው? ወይስ ፊቴን የሚቃወም እረኛ ማን ነው?

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ኤርምያስ 50:44
18 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

አቤቱ፥ ሰማያት ድንቅ ሥራህን ታማኝነትህንም፥ በቅዱሳን ማኅበር፥ ያመሰግናሉ።


በቅዱሳን ምክር እግዚአብሔር ክቡር ነው፥ በዙሪያው ባሉት ሁሉ ላይ ታላቅና ግሩም ነው።


ከአማልክት መካከል ጌታ ሆይ፥ እንደ አንተ ያለ ማን ነው? በቅድስና ባለግርማ፥ በምስጋና የተፈራህ፥ ድንቅንም የምታደርግ፥ እንደ አንተ ያለ ማን ነው?


እንግዲህ እግዚአብሔርን በማን ትመስሉታላችሁ? ወይስ በምን ምሳሌ ታስተያዩታላችሁ?


እንግዲህ የሚስተካከለኝ ማን አለ? ከማንስ ጋር አመሳሰላችሁኝ? ይላል ቅዱሱ።


አንዱን ከሰሜን አነሣሁ መጥቶአልም፤ አንዱም ከፀሐይ መውጫ ስሜን የሚጠራ ይመጣል፤ በጭቃ ላይ እንደሚመጣ ሰው አፈርም እንደሚረግጥ ሸክለኛ በአለቆች ላይ ይመጣል።


ታውቁና ታምኑብኝ ዘንድ እኔም እንደሆንሁ ታስተውሉ ዘንድ፥ እናንተ የመረጥሁትም አገልጋዬ ምስክሮቼ ናችሁ ይላል ጌታ፤ ከእኔ በፊት አምላክ አልተሠራም ከእኔም በኋላ አይኖርም።


ከምሥራቅ ነጣቂ ወፍን፥ ከሩቅም አገር ምክሬን የሚያደርገውን ሰው እጠራለሁ። ተናግሬአለሁ እፈጽምማለሁ፤ አስቤአለሁ አደርግማለሁ።


እኔ አምላክ ነኝና፥ ሌላም የለምና የቀድሞውን የጥንቱን ነገር አስቡ፤ እኔ እግዚአብሔር ነኝ እንደ እኔም ያለ ማንም የለም።


እናንተ ሁሉ፥ በአንድነት ተሰብስባችሁ ስሙ፤ ከእነርሱ ይህን የተናገረ ማን ነው? ጌታ የወደደው ፈቃዱን በባቢሎን ላይ ያደርጋል፥ ክንዱም በከለዳውያን ላይ ይሆናል።


“ከእግረኞች ጋር በሮጥህ ጊዜ እነርሱ ቢያደክሙህ፥ ከፈረሶች ጋር መታገል እንዴት ትችላለህ? በሰላምም ምድር ተሰናክለህ ከወደቅህ፥ በዮርዳኖስ ዱር እንዴት ታደርጋለህ?


እንደ ደቦል አንበሳ መደቡን ለቅቆአል፤ ከአስጨናቂውም ሰይፍና ከጽኑ ቁጣው የተነሣ ምድራቸው ባድማ ሆናለችና።”


አለቃቸው ከእነርሱ ውስጥ አንዱ ይሆናል፥ ገዥአቸውም ከመካከላቸው ይወጣል፤ እኔ አቀርበዋለሁ እርሱም ይቀርበኛል፤ ይህስ ባይሆን ለነፍሱ ዋስትና ሰጥቶ ወደ እኔ ለመቅረብ የሚደፍር ማን ነው? ይላል ጌታ።


የጌታ በቀል ነውና በዙሪያዋ ሆናችሁ በእርሷ ላይ ጩኹ፤ እጅዋን ሰጠች፤ ግንቦችዋ ወደቁ ቅጥሮችዋም ፈረሱ፤ እርሷን ተበቀሉ እንደ ሠራችውም ሥሩባት።


የእረኞች ክብር ተዋርዶአልና የዋይታቸውን ድምፅ ስሙ! የዮርዳኖስ ጥቅጥቅ ደን ወድሟልና የአንበሶች ግሣት ድምፅ ስሙ!


ለቆሬም እርሱንም ለተከሉት ሁሉ እንዲህ ቡሎ ተናገረ፦ “ነገ ጠዋት ጌታ ለእርሱ የሆነውን ሰው፥ ቅዱስም ማን እንሆነ፥ ወደ እርሱም ለመቅረብ የተፈቀደለትን ሰው ያሳውቃል፤ የመረጠውንም ሰው ወደ እርሱ እንዲቀርብ ይፈቅድለታል።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች