Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ኤርምያስ 50:36 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

36 ሰይፍ በምዋርተኞች ላይ አለ ሞኞችም ይሆናሉ፥ ሰይፍም በኃያላኖችዋ ላይ አለ እነርሱም ይጠፋሉ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

36 ሰይፍ በሐሰተኞች ነቢያቷ ላይ መጣ! እነርሱም ሞኞች ይሆናሉ፤ ሰይፍ በጦረኞቿ ላይ ተመዘዘ፤ እነርሱም ይሸበራሉ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

36 ሟርተኞቻቸው ሞኞች ይሆኑ ዘንድ ወታደሮቻቸውም በፍርሃት ይርበደበዱ ዘንድ ሰይፍ በእነርሱ ላይ ይመዘዝ!።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

36 ሰይፍ በተ​ዋ​ጊ​ዎ​ችዋ ላይ አለ፤ እነ​ር​ሱም ይደ​ክ​ማሉ። ሰይ​ፍም በኀ​ያ​ላ​ኖ​ችዋ ላይ አለ፤ እነ​ር​ሱም ይደ​ነ​ግ​ጣሉ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

36 ሰይፍ በሚጓደዱት ላይ አለ ሰነፎችም ይሆናሉ፥ ሰይፍም በኃያላኖችዋ ላይ አለ እነርሱም ይደነግጣሉ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ኤርምያስ 50:36
22 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

እነሆ፥ እንደ ንስር ወጥቶ ይበራል ክንፉንም በባሶራ ላይ ይዘረጋል፥ በዚያም ቀን የኤዶምያስ ኃያላን ልብ ምጥ እንደ ያዛት ሴት ልብ ይሆናል።”


እነሆ፥ በመካከልሽ ያለው ሕዝብሽ ሴቶች ናቸው፤ የምድርሽ በሮች ለጠላቶችሽ በሰፊው ተከፍተዋል፥ መወርወሪያዎችሽን እሳት በልቶአቸዋል።


የሐሰተኞችን ምልክት ከንቱ አደርጋለሁ፥ ምዋርተኞችንም አሳብዳለሁ፥ ጥበበኞቹንም ወደ ኋላ እመልሳለሁ፥ እውቀታቸውንም ስንፍና አደርጋለሁ፤


ውሻዎችና አስማተኞች፥ ሴሰኛዎችም፥ ነፍሰ ገዳዮችም፥ ጣዖት አምላኪዎችም፥ ውሸትንም የሚወዱና የሚያደርጉ ሁሉ በውጭ ይቀራሉ።


ነገር ግን የሚፈሩ፥ የማያምኑ፥ የሚረክሱ፥ ነፍሰ የሚያጠፉ፥ የሚሴሰኑ፥ አስማትን የሚያደርጉ፥ ጣዖትንም የሚያመልኩና የሚዋሹ ሁሉ ዕጣ ክፍላቸው በዲንና በእሳት በሚቃጠል ባሕር ውስጥ ነው፤ ይህም ሁለተኛው ሞት ነው።”


አውሬውም ተያዘ፤ በእርሱም ፊት ተአምራትን እያደረገ የአውሬውን ምልክት የተቀበሉትን ለምስሉም የሰገዱትን ያሳተ ሐሰተኛውም ነቢይ ከእርሱ ጋር ተያዘ፤ ሁለቱም በሕይወት ሳሉ በዲን ወደሚቃጠል ወደ እሳት ባሕር ተጣሉ።


በትዕቢት የተወጠረና ምንም የማያውቅ ነው፤ ነገር ግን የንትርክና በቃላት የመከራከር ለየት ያለ ክፉ ምኞት አለበት፤ እነዚህም ነገሮች የሚያመጡት ቅንዓትን፥ መከፋፈልን፥ ስድብን፥ ክፉ ጥርጣሬን፥


ይህም ትምህርት ኅሊናቸውን በጋለ ብረት በማቃጠል አደንዝዘው ውሸትን በሚናገሩ ግብዞች በኩል የሚሰጥ ነው፤


የሚያይሽም ሁሉ ከአንቺ ሸሽቶ፦ ነነዌ ወድማለች፤ ማን ያዝንላታል? አንቺን የሚያጽናኑ ከወዴት እፈልጋለሁ? ይላል።


ቆሟል፥ ተገለጠች፥ ተማረከች፥ ሴቶች አገልጋዮቿም እንደ ርግብ እየጮኹና ደረታቸውን እየመቱ አለቀሱ።


የወንዙም መሻገርያዎች ተይዘዋል፥ የውኃ ማቆርያዎቹም በእሳት ተቃጥለዋል ወታደሮቹም በሽብር ውስጥ ናቸው።


የባቢሎን ኃያላን መዋጋትን ትተዋል በምሽጎቻቸውም ውስጥ ተቀምጠዋል፤ ኃይላቸውም ደክሙአል እንደ ሴቶችም ሆነዋል፤ ማደሪያዎችዋም ነድደዋል መቀርቀሪያዎችዋም ተሰብረዋል።


በአንቺም እረኛውንና መንጋውን እሰባብራለሁ፤ በአንቺም አራሹንና ጥማጁን እሰባብራለሁ፤ በአንቺም ገዢዎችንና ሹማምቶችን አሰባብራለሁ።


ስለዚህ ጐልማሶችዋ በአደባባይዋ ላይ ይወድቃሉ፥ በዚያም ቀን ወታደርዎችዋ ሁሉ ይጠፋሉ፥ ይላል ጌታ።


እኔ እብሪቱን አውቃለሁ፥ ይላል ጌታ፤ ፉከራው ሐሰት ነው፥ ሥራውም ሐሰት ነው።


የእስራኤል ቅዱስ፥ የሚቤዣችሁ፥ ጌታ እንዲህ ይላል፦ ስለ እናንተ ወደ ባቢሎን ሰድጃለሁ፥ ከላዳውያንንም ሁሉ ስደተኞች አድርጌ በሚመኩባቸው መርከቦች አዋርዳቸዋለሁ።


እርሱም እየተናረ ሳለ ንጉሡ እንዲህ አለው፦ “በውኑ አንተ የንጉሡ አማካሪ ልትሆን ሾመነሃልን? ተው፤ እንዲገድሉህ ለምን ትሻለህ?” ነቢዩም፦ “ይህን አድርገሃልና፥ ምክሬንም አልሰማህምና ጌታ ሊያጠፋህ እንዳሰበ አወቅሁ” ብሎ ተወ።


አቤሴሎምና የእስራኤል ሰዎች ሁሉም “ከአኪጦፌል ምክር ይልቅ የአርካዊው የሑሻይ ምክር ይሻላል” አሉ፤ ጌታ በአቤሴሎም ላይ ጥፋት ለማምጣት፥ ጌታ መልካም የነበረው የአኪጦፌል ምክር ተቀባይነት እንዲያጣ አድርጎአል።


በዚህ ጊዜ፥ “ከአቤሴሎም ጋር ካሤሩት መካከል አንዱ አኪጦፌል ነው” ብለው ለዳዊት ነገሩት። ዳዊትም፥ “ጌታ ሆይ! እባክህን የአኪጦፌልን ምክር ወደ ከንቱነት ለውጠው” ሲል ጸለየ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች