Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ኤርምያስ 50:31 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

31 ትዕቢተኛው ሆይ! የመጐብኘትህ ጊዜ፥ ቀንህ ደርሶአልና እነሆ፥ በአንተ ላይ ነኝ፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

31 “አንተ ትዕቢተኛ፤ እነሆ፤ በአንተ ላይ ተነሥቻለሁ፤” ይላል የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር፤ “የምትቀጣበት ጊዜ፣ ቀንህ ደርሷልና።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

31 “ትዕቢተኛይቱ ባቢሎን ሆይ! እኔ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር በአንቺ ላይ እነሣለሁ፤ አንቺንም የምቀጣበት ጊዜ ደርሶአል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

31 ትዕ​ቢ​ተኛ ሆይ! አን​ቺን የሚ​በ​ቀ​ሉ​በት ጊዜ፥ ቀንሽ ደር​ሶ​አ​ልና እነሆ በአ​ንቺ ላይ ነኝ፥ ይላል የሠ​ራ​ዊት ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

31 ትዕቢተኛው ሆይ፥ የመጐብኘትህ ጊዜ፥ ቀንህ ደርሶአልና እነሆ፥ በአንተ ላይ ነኝ፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ኤርምያስ 50:31
20 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እብሪተኛውንና ትዕቢተኛውን ሁሉ፤ የተኩራራውን በሙሉ የሚያዋርድበት ቀን አለው።


እነሆ፥ በሸለቆው ውስጥ በሜዳ ላይም ባለው አምባ የምትቀመጪ ሆይ! እኔ በአንቺ ላይ ነኝ፥ ይላል ጌታ፤ እናንተም፦ ‘በእኛ ላይ የሚወርድ ወይም ወደ መኖሪያችን የሚገባ ማን ነው?’ የምትሉ ሆይ! እኔ በእናንተ ላይ ነኝ፤


እጅግ እንደ ታበየ ስለ ሞዓብ ትዕቢት ስለ ትምክህቱም ስለ ኩራቱም ስለ እብሪቱም ስለ ልቡም ትዕቢት ሰምተናል።


በዓለት ንቃቃት ውስጥ የምትቀመጥ፥ የተራራውን ከፍታ የምትይዝ ሆይ! ማሣቀቅያህና የልብህ ኩራት አታልለውሃል። ምንም እንኳ ጎጆህን እንደ ንስር ጎጆ ከፍ ብታደርግ፥ ከዚያ አወርድሃለሁ፥ ይላል ጌታ።


ቀስትን የሚገትሩትን ቀስተኞችን ሁሉ በባቢሎን ላይ ጥሩአቸው፤ በዙሪያዋ ስፈሩባት አንድም ሰው አያምልጥ፤ በእስራኤል ቅዱስ በጌታ ላይ በኩራት አልታዘዝም ብላለችና እንደ ሥራዋ መጠን መልሱላት፥ እንዳደረገችም ሁሉ አድርጉባት።


ትዕቢተኛው ተሰናክሎ ወድቆአ የሚያነሣውም ማንም የለም፤ በከተሞቹም ውስጥ እሳት አነድዳለሁ፥ በዙሪያውም ያለውን ሁሉ ትበላለች።


አንተ ምድርን ሁሉ የምታጠፋ አጥፊው ተራራ ሆይ! እነሆ፥ እኔ በአንተ ላይ ነኝ፥ ይላል ጌታ፤ እጄንም እዘረጋብሃለሁ፥ ከዓለትም ራስ ላይ አንከባልልሃለሁ፥ የተቃጠለም ተራራ አደርግሃለሁ።


እንዲህም ብለህ ተናገር፦ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “‘ወንዙ የእኔ ነው እኔ ራሴ ሠርቼዋለሁ’ የምትል፥ በወንዞች መካከል የምትተኛ፥ አንተ ታላቅ ድራጎን የግብጽ ንጉሥ ፈርዖን ሆይ፥ እነሆ በአንተ ላይ ነኝ።


እንዲህም በል፦ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ የሮሽ፥ የሜሼኽና የቱባል አለቃ ጎግ ሆይ፥ እነሆ እኔ በአንተ ላይ ነኝ።


አንተም፥ የሰው ልጅ ሆይ፥ በጎግ ላይ ትንቢትን ተናገር እንዲህም በል፦ አሁንም ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ የሞሼኽና የቱባል አለቃ ጎግ ሆይ፥ እነሆ፥ እኔ በአንተ ላይ ነኝ፥


ስለዚህ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እነሆ፥ እኔ ራሴ በአንቺ ላይ ነኝ፥ አገሮችም እያዩ በመካከልሽ ፍርድን አመጣብሻለሁ።


አንበሳው ለልጆቹ የሚበቃውን ያህል ነጠቀ፥ ለእንስቶቹም አነቀላቸው፥ ዋሻውን በነጠቀው፥ ጉድጓዱንም በተቦጫጨቀ ሥጋ ሞልቶታል።


እነሆ፥ በአንቺ ላይ ነኝ፥ ይላል የሠራዊት ጌታ፥ ልብስሽን እስከ ፊትሽ እገልጣለሁ፤ ኅፍረተ ሥጋሽን ለአሕዛብ፥ ነውርሽንም ለመንግሥታት አሳያለሁ።


ስለዚህ፥ “እግዚአብሔር ትዕቢተኞችን ይቃወማል፤ ለትሑታን ግን ጸጋን ይሰጣል” እንደሚል፥ የሚሰጠው ጸጋ ግን ከሁሉም ይበልጣል።


እንዲሁም እናንተ ጐልማሶች! ለሽማግሌዎች ተገዙ፤ ሁላችሁም ትሕትናን እንደ ልብስ ለብሳችሁ አንዱ ሌላውን ያገልግል፤ “እግዚአብሔር ትዕቢተኞችን ይቃወማል፤ ለትሑታኑ ግን ጸጋን ይሰጣል” ተብሎ ተጽፎአልና።


ስለዚህም ሞትና ኀዘን፥ ራብም የሆኑት መቅሰፍቶችዋ በአንድ ቀን ይመጣሉ፤ በእሳትም ትቃጠላለች፤ የሚፈርድባት ጌታ እግዚአብሔር ብርቱ ነውና።”


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች