ኤርምያስ 50:26 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)26 ከየአቅጣጫው በእርሷ ላይ ኑ፥ ጎተራዎችዋንም ክፈቱ፤ እንደ ተቈለለ ነዶ ከምርዋት ፈጽማችሁም አጥፉአት፥ ምንም ዓይነት ነገር አታስተርፉላት። ምዕራፉን ተመልከትአዲሱ መደበኛ ትርጒም26 ከሩቅ መጥታችሁ በርሷ ላይ ውጡ፤ ጐተራዎቿን አፈራርሱ፤ እንደ እህል ክምር ከምሯት፤ ፈጽማችሁ አጥፏት፤ ምኗም አይቅር። ምዕራፉን ተመልከትአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም26 ከየአቅጣጫው ዝመቱባት፤ እህልዋ የተከማቸበትን ጐተራ ሁሉ ክፈቱ፤ ምርኮውንም እንደ እህል ምርት ቈልሉት፤ ምንም ነገር ሳትተዉ አገሪቱን አጥፉ! ምዕራፉን ተመልከትየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)26 ጊዜዋ ደርሶአልና ሣጥኖችዋን ከፍታችሁ እንደ ዋሻ በርብሯት፤ ጨርሳችሁም አጥፏት፥ ምንም አታስቀሩላት። ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)26 ከየበኩሉ በእርስዋ ላይ ውጡ፥ ጎተራዎችዋንም ክፈቱ፥ እንደ ክምርም አድርጓት ፈጽማችሁም አጥፉአት፥ አንዳችም አታስቀሩላት። ምዕራፉን ተመልከት |