ኤርምያስ 50:16 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)16 ዘሪውንና በመከር ጊዜ ማጭድ የሚይዘውን ከባቢሎን አጥፉ፤ የአስጨናቂው ሰው ከሆነው ሰይፍ ፊት እያንዳንዱ ወደ ወገኑ ይመለሳል እያንዳንዱም ወደ አገሩ ይሸሻል። ምዕራፉን ተመልከትአዲሱ መደበኛ ትርጒም16 ከባቢሎን ዘር የሚዘራውን፣ በመከር ጊዜ ማጭድ የጨበጠውንም ዐጫጅ አጥፉት፤ ከአጥፊው ሰይፍ የተነሣ፣ እያንዳንዱ ወደ ገዛ ሕዝቡ ይመለስ፤ ወደ ገዛ ምድሩም ይሽሽ። ምዕራፉን ተመልከትአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም16 ዘሪውንና መከር ሰብሳቢውን ከባቢሎን አስወግዱ፤ በዚያች አገር የሚኖር እያንዳንዱ የውጪ ዜጋ አደጋ የሚጥልባትን ሠራዊት በመፍራት ወደ ወገኑ ይመለሳል፤ ወደ አገሩም ይሸሻል።” ምዕራፉን ተመልከትየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)16 ዘሪውንና በመከር ጊዜ ማጭድ የሚይዘውን ከባቢሎን አጥፉ፤ ከአረማዊው ሰይፍ ፊት የተነሣ እያንዳንዱ ወደ ወገኑ ይመለሳል፤ እያንዳንዱም ወደ ሀገሩ ይሸሻል። ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)16 ዘሪውንና በመከር ጊዜ ማጭድ የሚይዘውን ከባቢሎን አጥፉ፥ ከሚያስጨንቅ ሰይፍ ፊት እያንዳንዱ ወደ ወገኑ ይመለሳል እያንዳንዱም ወደ አገሩ ይሸሻል። ምዕራፉን ተመልከት |