ኤርምያስ 5:7 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)7 “በእነዚህ ነገሮች ይቅር የምልሽ እንዴት አድርጌ ነው? ልጆችሽ ትተውኛል፥ አማልክትም ባልሆኑ ምለዋል፤ ካጠገብኋቸውም በኋላ አመነዘሩ በጋለሞቶቹም ቤት ተሰበሰቡ። ምዕራፉን ተመልከትአዲሱ መደበኛ ትርጒም7 “ታዲያ፣ እንዴት ይቅር ልልሽ እችላለሁ? ልጆችሽ ትተውኛል፤ እውነተኛውን አምላክ ትተው አማልክት ባልሆኑት ምለዋል፤ እስኪጠግቡ ድረስ መገብኋቸው፤ እነርሱ ግን አመነዘሩ፤ ወደ ጋለሞቶችም ቤት ተንጋጉ። ምዕራፉን ተመልከትአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም7 እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “ሕዝቤ እኔን ትተው ሐሰተኞች አማልክትን ያመልካሉ፤ ታዲያ እኔ የእነርሱን ኃጢአት ይቅር የምለው ለምንድን ነው? እኔ ለሕዝቤ የሚያስፈልጋቸውን ምግብ ሁሉ በመስጠት እንዲጠግቡ አደረግሁ፤ እነርሱ ግን አመንዝሮች ሆኑ፤ ማደሪያቸውም በአመንዝሮች ቤት ሆነ። ምዕራፉን ተመልከትየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)7 “ከእነዚህ ነገሮች በየትኛው ይቅር እልሻለሁ? ልጆችሽ ትተውኛል፤ አማልክትም ባልሆኑ ምለዋል፤ አጠገብኋቸውም፤ እነርሱ ግን አመነዘሩ፤ በአመንዝራዎቹም ቤት ዐደሩ። ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)7 በእነዚህ ነገሮች ይቅር የምልሽ እንዴት አድርጌ ነው? ልጆችሽ ትተውኛል አማልክትም ባልሆኑ ምለዋል፥ ካጠገብኋቸውም በኋላ አመነዘሩ በጋለሞቶቹም ቤት ተሰበሰቡ። ምዕራፉን ተመልከት |