ኤርምያስ 49:31 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)31 “ተነሡ፥ በደኅንነት ተቀምጦ ተረጋግቶ ወዳለው፥ የቅጥር በርና መቀርቀሪያ ወደሌለው ብቻውንም ወደ ተቀመጠው ሕዝብ ውጡ፥ ይላል ጌታ። ምዕራፉን ተመልከትአዲሱ መደበኛ ትርጒም31 “ተነሡ፣ ተዘልሎ የተቀመጠውን፣ በራሱ ተማምኖ የሚኖረውን ሕዝብ ውጉ፤” ይላል እግዚአብሔር፤ “መዝጊያና መቀርቀሪያ በሌለው፤ ለብቻው በሚኖረው ሕዝብ ላይ ዝመቱ። ምዕራፉን ተመልከትአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም31 እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “ተነሡ! መዝጊያና መወርወሪያ ሳይኖረው ብቸኛ ሆኖ ወደሚኖርና ተዝናንቶ በሰላም ወደ ተቀመጠው ሕዝብ ዝመቱ። ምዕራፉን ተመልከትየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)31 “ተነሡ፤ ዕረፍት ወዳለበት፥ ተዘልሎም ወደ ተቀመጠው፥ ደጅና መዝጊያ፥ መወርወሪያም ወደሌለው፥ ብቻውንም ወደ ተቀመጠው ሕዝብ ዝመቱ። ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)31 ተነሡ፥ ዕርፊት ወዳለበት ተዘልሎም ወደ ተቀመጠው፥ ደጅና መወርወሪያ ወደሌለው ብቻውንም ወደ ተቀመጠው ሕዝብ ውጡ። ምዕራፉን ተመልከት |