Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ኤርምያስ 49:29 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

29 ድንኳኖቻቸውንና መንጋቸውን፥ መጋረጃዎቻቸውንና ዕቃዎቻቸውን ሁሉ ይወስዳሉ፤ ግመሎቻቸውንም ለራሳቸው እየነዱ ይወስዳሉ፥ እነርሱም፦ በዙሪያቸው ሁሉ ሽብር አለ፥ እያሉ ለእነርሱ ይጮኻሉ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

29 ድንኳኖቻቸውና መንጎቻቸው ይወሰዳሉ፤ መጠለያቸውና ግመሎቻቸው ሳይቀሩ፣ ከነዕቃዎቻቸው ይነጠቃሉ፤ ሰዎች፣ ‘ሽብር በሽብር ላይ መጥቶባቸዋል፤’ እያሉ ይጮኹባቸዋል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

29 ድንኳኖቻቸውን፥ መንጋዎቻቸውን፥ መጋረጃዎቻቸውንና ዕቃዎቻቸውን ሁሉ ውሰዱ፤ ግመሎቻቸውን ለራሳችሁ ውሰዱ። ‘በዙሪያው ሽብር ተነሥቷል’ ብለው ይጮኻሉ።”

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

29 ድን​ኳ​ና​ቸ​ው​ንና በጎ​ቻ​ቸ​ውን ይወ​ስ​ዳሉ፤ መጋ​ረ​ጃ​ዎ​ቻ​ቸ​ው​ንና ዕቃ​ቸ​ውን ሁሉ፥ ግመ​ሎ​ቻ​ቸ​ው​ንም ለራ​ሳ​ቸው ይወ​ስ​ዳሉ፤ በዙ​ሪ​ያ​ቸ​ውም ሁሉ ጥፋ​ትን ጥሩ​ባ​ቸው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

29 ድንኳናቸውንና መንጋቸውን ይወስዳሉ፥ መጋረጆቻቸውንና ዕቃቸውን ሁሉ ግመሎቻቸውንም ለራሳቸው ይወስዳሉ፥ በዙሪያቸውም ሁሉ ጥፋትን ጥሩባቸው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ኤርምያስ 49:29
21 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ፈርተው ወደ ኋላ ሲመለሱ፥ ኃያላኖቻቸውም ሲደበደቡ ወደ ኋላቸውም ሳይመለከቱ ፈጥነው ሲሸሹ ለምን አየሁ? በዚህና በዚያ ድንጋጤ አለ፥ ይላል ጌታ።


የጠላት ሰይፍና ድንጋጤ ከብበዋችኋልና ወደ ሜዳ አትውጡ በመንገድም ላይ አትሂዱ።


የኢትዮጵያ ድንኳኖች በጭንቀት ላይ ሆነው አየሁ፥ የሚድያን ምድር መጋረጃዎች ተንቀጠቀጡ።


መኖሪያዬ የራቀ እኔ ወዮልኝ፥ በቄዳር ድንኳኖች አደርሁ።


ወደ መቄዶንያም በመጣን ጊዜ፥ በሁሉ ነገር መከራን ተቀበልን እንጂ ሰውነታችን ዕረፍት አልነበረውም፤ ከውጭ ጠብ ነበረ፤ ከውስጥ ደግሞ ፍርሃት ነበረብን።


ከየአቅጣጫው መከራን እንቀበላለን እንጂ አንጨነቅም፤ ግራ እንጋባለን እንጂ ተስፋ አንቆርጥም፤


ደማስቆ ደከመች ለመሸሽም ዘወር አለች መንቀጥቀጥም ያዛት፥ እንደ ወላድም ሴት ጣርና ምጥ ያዛት።


ድንኳኔ ተበዘበዘ አውታሬም ሁሉ ተቈረጠ፤ ልጆቼም ከእኔ ወጥተው አይገኙም፤ ድንኳኔንም ከእንግዲህ ወዲህ የሚዘረጋ መጋረጃዎችንም የሚያነሣ የለም።


መከራ በመከራ ላይ ተጠርቶአል፤ ምድሪቱም ሁሉ ጠፍታለችና፤ በድንገትም ድንኳኔ በዐይን ቅጽበትም መጋረጃዎቼ ጠፉ።


የቄዳር መንጎች ሁሉ ወደ አንቺ ይሰበሰባሉ የነባዮትም አውራ በጎች ያገለግሉሻል፤ እኔን ደስ ሊያሰኙ በመሠዊያዬ ላይ ይወጣሉ፥ የክብሬንም ቤት አከብራለሁ።


በዘመናት ሁሉ የሚቀመጥባት አይኖርም፤ የሚቀመጥባትም የለም ዐረብ በዚያ ድንኳኑን አይተክልም፤ እረኛም መንጋውን በዚያ አያሳርፍም።


እንደ ሞተ ሰው ከልብ ተረሳሁ፥ እንደ ተበላሸ ዕቃም ሆንሁ።


ሰባት ሺህ በጎች፥ ሦስት ሺህ ግመሎች፥ አምስት መቶ ጥማድ በሬዎች፥ አምስት መቶ እንስት አህዮችና እጅግ ብዙም አገልጋዮች ነበሩት። ያም ሰው በምሥራቅ ካሉ ሰዎች ሁሉ ይልቅ ታላቅ ነበረ።


ሌሎቹን ጌጣ ጌጦች ይኸውም የአንገት ሐብሉን ከነእንጥልጥሉ፥ የምድያም ነገሥታት ይለብሱት የነበረውን ሐምራዊ ልብስ ወይም በግመሎቻቸው አንገት ላይ ያሉትን ጌጦች ሳይጨምር ጌዴዎን በጠየቃቸው መሠረት የሰጡት የወርቅ ጉትቻ ክብደት ሺህ ሰባት መቶ ሰቅል ያህል መዘነ።


ዜባሕና ጻልሙናም፥ “የሰው ጉልበቱ እንደ ሰውነቱ መጠን ነውና፥ አንተው ራስህ ግደለን አሉት፤” ጌዴዎንም ተነሥቶ ገደላቸው፤ በግመሎቻቸው አንገት ላይ የነበሩትንም ጌጦች ወሰደ።


ብዛታቸው እንደ አንበጣ መንጋ የሆነ ምድያማውያን፥ አማሌቃውያንና ሌሎችም የምሥራቅ ሕዝቦች በሸለቆው ውስጥ ሰፍረው ነበር፤ የግመሎቻቸውም ብዛት በባሕር ዳርቻ እንዳለ አሸዋ ስፍር ቍጥር አልነበረውም።


ከብቶቻቸውንና ድንኳኖቻቸውን ይዘው ሲመጡ ልክ የአንበጣ መንጋ ይመስሉ ነበር፤ ሰዎቹንም ሆነ ግመሎቻቸውን ለመቁጠር አዳጋች ሲሆን፥ የሚመጡትም ምድሪቱን ለማጥፋት ነበር።


ምግብ ሊበሉ ተቀመጡ፥ ዓይናቸውንም አንሥተው ሲያዩ፥ እነሆ የእስማኤላውያን ነጋዴዎች ወደ ግብጽ ለመውረድ ከገለዓድ ይመጣሉ፥ ግመሎቻቸውም ሽቱና በለሳን፥ ከርቤም ተጭነው ነበር።


እነሆ፥ በዙሪያሽ ካሉት ሁሉ ዘንድ በአንቺ ላይ ፍርሃትን አመጣብሻለሁ፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር፤ እያንዳንዳችሁም በፊታችሁ ወዳለው ስፍራ ትሰደዳላችሁ፥ የሚሸሹትንም የሚሰበስብ የለም።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች